Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 21:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ብንያማውያንም ተመልሰው መጡ፤ ሌሎቹም እስራኤላውያን ከሞት በመትረፍ ከያቤሽ ተማርከው የመጡትን ልጃገረዶች ሰጡአቸው፤ ነገር ግን ቊጥራቸው ተመጣጣኝ ሆኖ አልተገኘም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቍጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህ በዚህን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቊጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በዚ​ያም ጊዜ የብ​ን​ያም ልጆች ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሴቶች ያዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን ሴቶች ሰጡ​አ​ቸው። በዚ​ህም ተስ​ማሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ተመለሱ፥ ከኢያቢስ ገለዓድም ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች አገቡአቸው። ነገር ግን የሚበቁ ሴቶች አላገኙም።

参见章节 复制




መሳፍንት 21:14
7 交叉引用  

ነገር ግን ከዝሙት ለመራቅ እያንዳንዱ ወንድ የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዱዋም ሴት የራስዋ ባል ይኑራት።


ነገር ግን ወደ በረሓው፥ የሪሞን አለት ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ በመሸሽ ለማምለጥ የቻሉት ስድስት መቶ ሰዎች ብቻ ነበሩ። እነርሱም በዚያ አራት ወር ቈዩ።


በዚህም ዐይነት በያቤሽ ገለዓድ ካሉት ኗሪዎች መካከል አራት መቶ ወንድ ያላወቁ ቆነጃጅት አገኙ፤ ስለዚህም እነርሱን በከነዓን ምድር በሴሎ ወደሚገኘው ሰፈር ይዘው መጡ።


ከዚህ በኋላ መላው ጉባኤ የሪሞን አለት ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ወደነበሩት ብንያማውያን መልእክት ልከው ጦርነቱ እንዲቆም ተስማሙ፤


እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ነገዶች መካከል ያለው አንድነት እንዲቋረጥ አድርጎ ስለ ነበር ሕዝቡ ስለ ብንያማውያን እጅግ አዘኑ።


አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ወደ እናንተ መጥተው ሊቃወሙአችሁ ቢፈልጉ ‘ሚስቶች ለማድረግ የወሰድናቸው በጦርነት አስገድደን ስላልሆነ እባካችሁ ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም በፈቃዳችሁ ስላልሰጣችሁን መሐላችሁን በማፍረስ በደለኞች አትሆኑም’ ብላችሁ መልስ መስጠት ትችላላችሁ።”


እነርሱ እንዲህ አሉ፦ “ከእስራኤል ነገዶች መካከል ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ያልመጣ አለን?” እነሆ ከያቤሽ ገለዓድ ወደ ስብሰባው ማንም አልመጣም ነበር።


跟着我们:

广告


广告