Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 20:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 በዚያን ቀን በአጠቃላይ የተገደሉት ብንያማውያን ኻያ አምስት ሺህ ሲሆኑ ሁሉም ምርጥ ጦረኞች ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 በዚያች ዕለት ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ዐምስት ሺሕ ብንያማውያን በጦር ሜዳ ወደቁ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 በዚያች ዕለት ሰይፍ የታጠቊ ሃያ አምስት ሺህ ብንያማውያን በጦር ሜዳ ወደቊ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 እን​ዲ​ሁም በዚያ ቀን ከብ​ን​ያም የሞ​ቱት ሃያ አም​ስት ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ እነ​ዚህ ሁሉ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 እንዲሁም በዚያ ቀን ከብንያም የሞቱት ሀያ አምስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፥ እነዚህ ሁሉ ጽኑዓን ነበሩ።

参见章节 复制




መሳፍንት 20:46
5 交叉引用  

በዚያን ቀን ብንያማውያን፥ ከየከተሞቻቸው ኻያ ስድስት ሺህ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎችን አሰባሰቡ፤ ይህም ከጊብዓ ኗሪዎች ከተመረጡት ከሰባት መቶ ሰዎች ሌላ ነው።


እግዚአብሔርም እስራኤልን በብንያማውያን ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረገ። በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከብንያም ወገን ኻያ አምስት ሺህ አንድ መቶ የጦር መሣሪያ የታጠቁ ሠራዊትን ገደሉ።


የቀሩት ወደ ኋላቸው ተመልሰው ወደ በረሓው፥ ወደ ሪሞን አለት በሸሹ ጊዜ በአውራው ጐዳና ላይ አምስት ሺህ ተገደሉ፤ እስከ ጊድዖም ድረስ ተሳደው ሁለት ሺህ ተገደሉ።


ነገር ግን ወደ በረሓው፥ የሪሞን አለት ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ በመሸሽ ለማምለጥ የቻሉት ስድስት መቶ ሰዎች ብቻ ነበሩ። እነርሱም በዚያ አራት ወር ቈዩ።


ሳኦልም “እኔ ከእስራኤል ነገዶች መካከል በተለይ ታናሽ የሆነው የብንያም ነገድ ተወላጅ ነኝ፤ በዚሁም ነገድ ውስጥ እንኳ የእኔ ቤተሰብ በጣም አነስተኛ ነው፤ ታዲያ እንዲህ ያለውን ጉዳይ ለእኔ ስለምን ትነግረኛለህ?” ሲል መለሰለት።


跟着我们:

广告


广告