Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 20:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ከእስራኤል በልዩ ሁኔታ የተመረጡት ዐሥር ሺህ ሰዎች በጊብዓ ላይ አደጋ ጣሉ፤ ውጊያውም ከባድ ሆነ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ብንያማውያን በቅርብ ጊዜ ችግር እንደሚደርስባቸው አልተገነዘቡም ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ከዚያም ከመላው እስራኤል የተውጣጣው ዐሥር ሺሕ ጦር በጊብዓ ላይ ፊት ለፊት አደጋ ጣለ። ውጊያው ከመበርታቱ የተነሣም፣ ብንያማውያን መጥፊያቸው እየቀረበ መምጣቱን ገና አላወቁም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ከዚያም ከመላው እስራኤል የተውጣጣው ዐሥር ሺህ ጦር በጊብዓ ላይ ፊት ለፊት አደጋ ጣለ። ውጊያው ከመበርታቱ የተነሣም፥ ብንያማውያን መጥፊያቸው እየቀረበ መምጣቱን ገና አላወቁም ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የተ​መ​ረጡ ዐሥር ሺህ ሰዎች ወደ ገባ​ዖን አን​ጻር መጡ፤ ውጊ​ያ​ውም በር​ትቶ ነበር፤ መከ​ራም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አላ​ወ​ቁም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ከእስራኤልም ሁሉ የተመረጡ አሥር ሺህ ሰዎች ወደ ጊብዓ አንጻር መጡ፥ ሰልፍም በርትቶ ነበር፥ መከራም እንዲያገኛቸው አላወቁም ነበር።

参见章节 复制




መሳፍንት 20:34
12 交叉引用  

ዕድሜአቸውን በተድላ ደስታ ያሳልፋሉ፤ ያለ ሥቃይም ከዚህ ዓለም በሞት ይለያሉ።


ክፉ ሰው የገዛ ኃጢአቱ ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል፥ ደግ ሰው ግን እየዘመረ ሐሤትን ያደርጋል።


የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ይወድቃሉ፤ የመውደቂያቸው ምክንያት ምን እንደ ሆነ አያውቁም።


ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሰው ይህ መጥፎ ዕድል መቼ እንደሚገጥመው አያውቅም፤ ወፍ በራ በወጥመድ ውስጥ እንደምትገባ፥ ዓሣም በመጥፎ አጋጣሚ በመረብ እንደሚያዝ እንዲሁም የሰው ልጅ ሁሉ ሳያስበው ድንገት በሚደርስበት በክፉ አጋጣሚ ይጠመዳል።


በመተትሽ ልታስወግጂ የማትችይው ክፉ ነገር ይመጣብሻል፤ ልትከላከዪ የማትችይው ችግር ይደርስብሻል፤ ምንም ያላሰብሽው ጥፋት በድንገት ያጋጥምሻል።


እንዲሁም የሰው ልጅ በማታስቡት ሰዓት ስለሚመጣ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ።”


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።


ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።


የዐይ ንጉሥ ይህን በአየ ጊዜ እርሱና የከተማው ሕዝብ እስራኤልን በጦርነት ለመግጠም ወደ ዓራባ ፊት ለፊት ወጡ። ከከተማው በስተጀርባ በኩል የደጀን ጦር መኖሩን አላወቁም ነበር።


እግዚአብሔርም እስራኤልን በብንያማውያን ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረገ። በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከብንያም ወገን ኻያ አምስት ሺህ አንድ መቶ የጦር መሣሪያ የታጠቁ ሠራዊትን ገደሉ።


跟着我们:

广告


广告