መሳፍንት 20:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 ብንያማውያን ሠራዊቱን እየተከተሉ በወጡ ጊዜ ከከተማው ርቀው ሄዱ፤ በዋናው መንገድ ላይ እንደበፊቱ በሠራዊቱ ላይ አደጋ መጣል ጀመሩ፤ ወደ ቤትኤልና ወደ ጊብዓ በሚወስዱት መንገዶችና በሜዳው ላይ ሠላሳ እስራኤላውያንን ገደሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም31 ብንያማውያንም ሊገጥሟቸው ወጡ፤ ከከተማዪቱም ርቀው እንዲሄዱ ተደረጉ፤ እንደ በፊቱም እስራኤላውያንን ይገድሉ ጀመር። ከዚህ የተነሣም በሜዳው እንዲሁም ወደ ቤቴልና ወደ ጊብዓ በሚወስደው መንገዶች ላይ ሠላሳ ያህል ሰዎች ወድቀው ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 ብንያማውያንም ሊገጥሟቸው ወጡ፤ ከከተማይቱም ርቀው እንዲሄዱ ተደረጉ፤ እንደ በፊቱም እስራኤላውያንን ይገድሉ ጀመር። ከዚህ የተነሣም በሜዳው እንዲሁም ወደ ቤቴልና ወደ ጊብዓ በሚወስደው መንገዶች ላይ ሠላሳ ያህል ሰዎች ወድቀው ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 የብንያምም ልጆች በሕዝቡ ላይ ወጡ፤ ከከተማዪቱም ሸሹ፤ እንደ ቀድሞውም ጊዜ፥ በአውራዎቹ መንገዶች፥ አንደኛው ወደ ቤቴል፥ ሁለተኛውም ወደ ገባዖን ሜዳ በሚወስዱት መንገዶች ላይ ሕዝቡን ይመቱ፥ ይገድሉም ጀመር፤ ከእስራኤልም ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 የብንያምም ልጆች በሕዝቡ ላይ ወጡ፥ ከከተማይቱም ተሳቡ፥ እንደ ቀድሞውም ጊዜ፥ በአውራዎቹ መንገዶች፥ አንደኛው ወደ ቤቴል ሁለተኛውም ወደ ጊብዓ ሜዳ በሚወስዱት መንገዶች ላይ፥ ሕዝቡን ይመቱ ይገድሉም ጀመር፥ ከእስራኤልም ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎችን ገደሉ። 参见章节 |