መሳፍንት 20:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 በዚያን ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ስለ ነበረ እግዚአብሔርን ጠየቀ፦ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንውጣን ወይስ እንቅር” ብሎ ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ነገ በእነርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጁ አደርጋለሁና ሂዱና ውጉአቸው!” አለ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም28 የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በፊቱ ይቆም ነበር። እስራኤላውያንም፣ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን እንደ ገና ሄደን ጦርነት እንግጠማቸው ወይስ ይቅር?” ሲሉ ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “ሂዱ፤ በነገው ዕለት በእጃችሁ እሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 የአሮን ልጅ፤ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በፊቱ ይቆም ነበር። እስራኤላውያንም፥ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን እንደገና ሄደን ጦርነት እንግጠማቸው ወይስ ይቅር?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ሂዱ፤ በነገው ዕለት በእጃችሁ እሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 በዚያም ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በፊቷ ይቆም ነበርና። “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንውጣን? ወይስ እንቅር?” አሉ። እግዚአብሔርም፥ “ነገ በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጡ” አላቸው። 参见章节 |