Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እንዲያውም እነዚህ የእስራኤል ሕዝብ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው መንገዴን ይከተሉ ወይም አይከተሉ እንደሆን የማውቀው በእነዚህ ሕዝቦች መሣሪያነት በመፈተን ነው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይህን የማደርገውም አባቶቻቸው እንዳደረጉት ሁሉ፣ እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን መንገድ የሚጠብቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማወቅ እፈትናቸው ዘንድ እነርሱን መሣሪያ ለማድረግ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ይህን የሚያደርገውም አባቶቻቸው እንዳደረጉት ሁሉ፥ እስራኤላውያን የጌታን መንገድ የሚጠብቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማወቅ እፈትናቸው ዘንድ እነርሱን መሣሪያ ለማድረግ ነው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ጠበቁ፥ ይሄ​ዱ​ባት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ወይም አይ​ጠ​ብቁ እንደ ሆነ እስ​ራ​ኤ​ልን እፈ​ት​ን​ባ​ቸው ዘንድ፤”

参见章节 复制




መሳፍንት 2:22
12 交叉引用  

ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ።


ነገር ግን የባቢሎን መልእክተኞች በአገሪቱ ስለ ተደረገው አስደናቂ ነገር ሊጠይቁት ወደ እርሱ መጥተው በነበረ ጊዜ እግዚአብሔር በሕዝቅያስ ልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ለማወቅ ይፈትነው ዘንድ ተወው።


እርሱ እርምጃዬን ሁሉ ያውቃል፤ ቢፈትነኝም እንደ ወርቅ ንጹሕ ሆኜ ያገኘኛል።


አምላክ ሆይ! ብር በእሳት ተፈትኖ እንደሚጠራ ፈተንከን።


ሙሴም በብርቱ ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አንድ እንጨት አሳየው፤ እርሱንም ወስዶ በውሃው ላይ በጣለው ጊዜ፥ ውሃው ወደጣፋጭነት ተለወጠ። በዚያ ስፍራ እግዚአብሔር የሚተዳደሩበት ደንብና ሥርዓት ሰጣቸው፤ በዚያም ፈተናቸው።


ወርቅና ብር በእሳት እንደሚፈተን እግዚአብሔርም የሰውን ልብ ይፈትናል።


እግዚአብሔር አምላካችሁ በፍጹም ልባችሁ ትወዱት እንደ ሆነ ለማወቅ ፈልጎ ልኮት ይሆናልና ያን ነቢይ ወይም አላሚ አትስሙት።


ሊያዋርድህና ሊፈትንህ፥ በመጨረሻም መልካም ነገር ሊያደርግልህ የቀድሞ አባቶችህ ተመግበው የማያውቁትን መና በምድረ በዳ ሰጠህ።


አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ለኢያሱ አሳልፎ በመስጠት እነዚያን ሕዝቦች በአንድ ጊዜ አላስወጣቸውም።


跟着我们:

广告


广告