Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 2:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ስለዚህ ኢያሱ በሞተ ጊዜ በምድሪቱ የነበሩትን ሰዎች አንዳቸውንም አላስወጣላቸውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው በምድሪቱ ከነበሩት ሕዝቦች አንዳቸውንም እንኳ በፊታቸው አሳድጄ አላስወጣም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው በምድሪቱ ከነበሩት ሕዝቦች አንዳቸውንም በፊታቸው አሳድጄ አላስወጣም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እኔም የነዌ ልጅ ኢያሱ ትቶ​አ​ቸው ከአ​ለፈ አሕ​ዛብ አን​ዱን ሰው እን​ኳን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከፊ​ታ​ቸው አላ​ወ​ጣም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21-22 ይሄዱባት ዘንድ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ወይም አይጠብቁ እንደ ሆነ እስራኤልን እፈትንባቸው ዘንድ፥ ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው አሕዛብ አንዱን ሰው እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ ከፊታቸው አላወጣም።

参见章节 复制




መሳፍንት 2:21
8 交叉引用  

ይህንንም ያደረግኹት ሕጌን ስለ ተላለፉ፥ ሥርዓቴንም ስላልተከተሉ፥ ሰንበትን ስላረከሱ፥ የቀድሞ አባቶቻቸውንም ጣዖቶች ስለ አመለኩ ነው።


አምላካችሁ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ከፊታችሁ ማባረሩን እንደማይቀጥል በእርግጥ ዕወቁ፤ እንዲያውም አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር እስክትጠፉ ድረስ እነዚህን ሕዝቦች ለጀርባችሁ መግረፊያ፥ ለዐይኖቻችሁ እንደሚወጋ እሾኽ፥ እንዲሁም አደገኛ ወጥመድና መውደቂያ ጒድጓድ ይሆኑባችኋል።


እኔም ገና ድል ያልተመቱትና ድል የመታኋቸው ሕዝቦች ይዞታ የነበረውና በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ወንዝ በመዋሰን በስተምዕራብ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር የሚደርሰውን ሁሉ ለነገዶቻችሁ ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤


አምላካችሁ እግዚአብሔር እነርሱን በፊታችሁ እንዲሸሹ ያደርጋል፤ እነርሱን ነቃቅሎ ያጠፋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁም ተስፋ መሠረት ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።


ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ “በከነዓናውያን ላይ አደጋ ለመጣል ከነገዶቻችን መካከል ተቀዳሚ ሆኖ ማን ይዝመት?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ።


ስለዚህ አሁን እነዚህን ሕዝቦች ከፊታችሁ እንደማላስወጣቸው እነግራችኋለሁ፤ እነርሱ ለእናንተ ጠላቶች ይሆናሉ፤ ባዕዳን አማልክታቸውም ወጥመድ ይሆኑባችኋል።”


በከነዓን ምድር ጦርነት ያልተለማመዱ እስራኤላውያንን ለመፈተን እግዚአብሔር በምድሪቱ የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው።


በምድሪቱ ላይ የቀሩትም፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መሪዎች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከባዓልሔርሞን ተራራ አንሥቶ እስከ ሐማት ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች የሚኖሩት ሒዋውያን ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告