Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 2:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ወደ ጦርነት በሄዱም ቊጥር ቀደም ብሎ በመሐላ በተናገረው መሠረት እግዚአብሔር ራሱ ይቃወማቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እነርሱ በብርቱ ጭንቀት ላይ ወደቁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እስራኤላውያን ለውጊያ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር አስቀድሞ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረውና እንደ ማለው ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ ትከፋባቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እጅግ ተጨነቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እስራኤላውያን ለውጊያ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ አስቀድሞ በእነርሱ ላይ እንደተናገረውና እንደማለው እንዲሸነፉ የጌታ እጅ ትከፋባቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እጅግ ተጨነቁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እንደ ማለ፥ ወደ ወጡ​በት ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትከ​ፋ​ባ​ቸው ነበ​ረች፤ እጅ​ግም ተጨ​ነቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ እንደማለ፥ ወደ ወጡበት ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ ትከፋባቸው ነበረች፥ እጅግም ተጨነቁ።

参见章节 复制




መሳፍንት 2:15
19 交叉引用  

የሮብዓም መንግሥት በጽኑ በተመሠረተና ኀይል ባገኘ ጊዜ እርሱና እስራኤላውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ፤


ያ ሕዝብ ተጸጽቶ ከክፋቱ የሚመለስ ከሆነ፥ አመጣበታለሁ ብዬ ያቀድኩትን ክፉ ነገር አላደርግበትም።


ይህች ከተማ እንድትጠፋ ወስኛለሁ፤ ፈጽሞም ምሕረት አላደርግላትም፤ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


“ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ በእናንተ ላይ በቊጣ ተነሣሥቼ ይሁዳን በሙሉ እደመስሳለሁ፤


ደግ ነገር ሳይሆን ክፉ ነገር እንዲደርስባችሁ አደርጋለሁ፤ ከእናንተ አንድ እንኳ ሳይተርፍ ሁላችሁም በጦርነትና በረሀብ ትሞታላችሁ፤


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ በእናንተ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፤ ከዚህም ልታመልጡ ፈጽሞ አትችሉም፤ ያ አሠቃቂ ጊዜ ስለሚሆን በትዕቢት መመላለስ አትችሉም።


በየአቅጣጫው መከራ ይደርስብናል፤ ግን አንሸነፍም፤ ብዙ ጊዜ ግራ ይገባናል፤ ግን ተስፋ አንቈርጥም፤


ነገር ግን ያላዘዝኩትን ማንኛውንም ነገር በስሜ መናገር የሚደፍር ነቢይ፥ ወይም በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ይገደል።


ዐሞናውያን የይሁዳን፥ የብንያምንና የኤፍሬምን ነገዶች ለመውጋት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ እስራኤላውያንም እጅግ ተጨነቁ።


እነርሱ ለአካለ መጠን እስኪደርሱ መጠበቅ ትችላላችሁን? በዚህስ ምክንያት ሌሎች ባሎች ሳታገቡ ትቀራላችሁን? ልጆቼ ሆይ! ይህ የማይሆን ነው፤ እኔን እግዚአብሔር ተቈጥቶኛል፤ በእናንተም ላይ በደረሰው ነገር በጣም አዝኜአለሁ” አለቻቸው።


ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባታዳምጡ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር ቅጣት ይበረታባችኋል፤


እስራኤላውያን ሁኔታው አስጊ መሆኑን ባዩና ሠራዊቱም መዋከቡን በተመለከቱ ጊዜ በዋሻ፥ በሾኽ ቊጥቋጦ፥ በአለቶች መካከል በጒድጓዶችና በጒድባ ውስጥ ተሸሸጉ፤


በዚያን ቀን እስራኤላውያን በራብ ደከሙ፤ ምክንያቱም ሳኦል “ጠላቶቼን እስክበቀል ድረስ ዛሬ እህል ውሃ የሚቀምስ ማናቸውም ሰው የተረገመ ይሁን!” ብሎ ሕዝቡን በማስማል ማንም ሰው እህል ውሃ እንዳይቀምስ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። ከዚህም የተነሣ ሁሉም ምንም ነገር ሳይቀምሱ ቀኑን ሙሉ ዋሉ።


ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤


跟着我们:

广告


广告