Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በአራተኛው ቀን ጧት በማለዳ ተነሡና ለመሄድ ተዘጋጁ፤ የልጅቱ አባት ግን የልጁን ባል “ብርታት እንድታገኝ መጀመሪያ እህል ቅመስ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳለህ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፤ እንግዳውም ለመሄድ ተዘጋጀ፤ የልጅቱ አባት ግን፣ “እንድትበረታ እህል ቅመስ፤ ከዚያም መሄድ ትችላለህ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፤ እንግዳውም ለመሄድ ተዘጋጀ፤ የልጂቱ አባት ግን፥ “እንድትበረታ እህል ቅመስ፤ ከዚያም መሄድ ትችላለህ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ማል​ደው ተነሡ፤ እር​ሱም ለመ​ሄድ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት አማ​ቹን፥ “ሰው​ነ​ት​ህን በቁ​ራሽ እን​ጀራ አበ​ርታ፤ ከዚ​ያም በኋላ ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፥ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፥ የብላቴናይቱም አባት አማቹን፦ ሰውነትህን በቁራሽ እንጀራ አበርታ፥ ከዚያም በኋላ ትሄዳለህ አለው።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:5
9 交叉引用  

ወደ እኔ ወደ አገልጋያችሁ በመምጣታችሁ ደስ ብሎኛል፤ ስለዚህ ለጒዞአችሁ ብርታት የሚሰጣችሁን ጥቂት ምግብ አምጥቼ እንዳስተናግዳችሁ ፍቀዱልኝ።” እነርሱም “መልካም ነው፤ እንዳልከው አድርግ” አሉት።


ከዚህም በኋላ ንጉሡ ነቢዩን “ና ከእኔ ጋር አብረህ ወደ ቤቴ ግባ፤ እህልም ቅመስ፤ ስጦታ እሰጥሃለሁ” አለው።


ስለዚህ ልቡን ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፥ ፊቱን የሚያበራ ዘይትና ብርታት የሚሰጠውን ምግብ ያዘጋጃል።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው።


መብልም በላና በረታ፤ በደማስቆ ከነበሩት ደቀ መዛሙርት ጋር ለጥቂት ቀኖች ቈየ።


እዚያ እንዲቈይ አደረገው፤ እርሱም ሦስት ቀን በዚያ ቈየ፤ እዚያም እየበሉና እየጠጡ ቈዩ።


በአምስተኛው ቀን ጧት በማለዳ ተነሥቶ ጒዞ ጀመረ፤ የልጅቱ አባት ግን “እባክህ እህል ቅመስ፤ ቈየት ብለህ ትሄዳለህ” አለው፤ ስለዚህም ሁለቱ ሰዎች አብረው በሉ።


ደረቅ የበለስ ፍሬና ሁለት ጥፍጥፍ ዘቢብ አቀረቡለት፤ ወጣቱም ከተመገበ በኋላ እንደገና በረታ፤ ከዚያ በፊት ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እህል ውሃ አልቀመሰም ነበር።


跟着我们:

广告


广告