Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ከዚያ በኋላ የላካቸውን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ለእስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ በሉአቸው፦ ‘የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ተደርጎ ያውቃልን? አስቡበት፤ ተመካከሩበት ተነጋገሩበትም።’ ” ያዩት ሁሉ “እስከዚህ ጊዜ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ታይቶም አይታወቅ!” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ያየም ሁሉ፣ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩበት” ተባባሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ያየም ሁሉ፥ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩ በት” ተባባሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከዚ​ያም በኋላ ያያት ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲህ ያለ ነገር የሆ​ነ​በት ጊዜ የለም፤ የታ​የ​በ​ትም ጊዜ የለም፤” ያም ሰው እነ​ዚ​ያን የላ​ካ​ቸ​ውን ሰዎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች እን​ዲህ በሏ​ቸው፦ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እን​ዲህ የሆ​ነ​በት ጊዜ አለን? እና​ንተ ተመ​ካ​ከ​ሩ​በት፤ የሚ​በ​ጀ​ው​ንም ተነ​ጋ​ገሩ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ያየም ሁሉ፦ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልተደረገም፥ አልታየምም፥ አስቡት፥ በዚህም ተመካከሩ፥ ተነጋገሩም ይባባል ነበር።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:30
7 交叉引用  

አማካሪ የሌለው መንግሥት ይወድቃል፤ ብዙ አማካሪዎች ሲኖሩ ግን ዋስትና ይገኛል።


ትዕቢት ጠብን ያመጣል፤ ምክርን መጠየቅ ግን ብልኅነት ነው።


መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ምክርን ባትቀበል ግን ምንም ነገር አይሳካልህም።


መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ስለዚህ መልካም ምክር ሳትቀበል ወደ ጦርነት አትሂድ።


ለጦርነት ከመሰለፍህ በፊት በጥንቃቄ ዕቅድ ማውጣት ይኖርብሃል፤ ብዙ አማካሪዎች የምታገኝ ከሆነም ማሸነፍህ አይቀርም።


የእስራኤል ሕዝብ በገባዖን ዘመን እንደ ነበሩት ሰዎች በጣም ረክሰዋል፤ እግዚአብሔርም በደላቸውን አስቦ ስለ ኃጢአታቸው ይቀጣቸዋል።


እዚህ ያላችሁት እስራኤላውያን ሁሉ ምክራችሁንና ፍርዳችሁን ስጡ።”


跟着我们:

广告


广告