Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሰዎቹ ግን አልሰሙትም፤ ስለዚህ ሰውዬው ቊባቱን ወደ ውጪ አውጥቶ ሰጣቸው፤ ሌሊቱንም ሙሉ በእርስዋ ላይ ተራ በተራ በማመንዘር መጫወቻ አድርገዋት ዐደሩ፤ ሲነጋጋ ግን እንድትሄድ ለቀቁአት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሆኖም ሰዎቹ ሊሰሙት አልፈለጉም፤ ስለዚህ ሌዋዊው ቁባቱን ወደ ውጭ አወጣላቸው፤ ሰዎቹም አመነዘሩባት፤ ሌሊቱን ሙሉ ሲፈራረቁባት ዐድረው ጎሕ ሲቀድ ለቀቋት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሆኖም ሰዎቹ ሊሰሙት አልፈለጉም፤ ስለዚህ ሌዋዊው ቁባቱን ወደ ውጭ አወጣላቸው፤ ሰዎቹም አመነዘሩባት፤ ሌሊቱን ሙሉ ሲፈራረቁባት አድረው ጐሕ ሲቀድ ለቀቋት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሰዎቹ ግን ሊሰ​ሙት አል​ፈ​ቀ​ዱም፤ ሰው​የ​ውም ዕቅ​ብ​ቱን ይዞ ወደ እነ​ርሱ አወ​ጣ​ላ​ቸው፤ አዋ​ረ​ድ​ዋ​ትም፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ እስ​ኪ​ነጋ ድረስ አመ​ነ​ዘ​ሩ​ባት፤ ጎህም በቀ​ደደ ጊዜ ለቀ​ቁ​አት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሰዎቹ ግን ነገሩን አልሰሙም፥ ሰውዮውም ቁባቱን ይዞ አወጣላቸው፥ ደረሱባትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፥ ጎህ በቀደደም ጊዜ ለቀቁአት።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:25
9 交叉引用  

አዳም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “በእግዚአብሔር ርዳታ ወንድ ልጅ አገኘሁ” ስትል “ቃየል” የሚል ስም አወጣችለት።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ በጊብዓ ኃጢአት ከሠሩበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ከማሳዘን አልተቈጠቡም፤ ስለዚህ በገባዖን ጦርነት ይነሣባቸዋል።


የእስራኤል ሕዝብ በገባዖን ዘመን እንደ ነበሩት ሰዎች በጣም ረክሰዋል፤ እግዚአብሔርም በደላቸውን አስቦ ስለ ኃጢአታቸው ይቀጣቸዋል።


የዕፍረት ስሜታቸው ስለ ጠፋ ርኲሰቶችን ሁሉ ለመፈጸም ራሳቸውን ለሥጋዊ ምኞታቸው አሳልፈው ሰጥተዋል።


እነሆ የሰውዬው ቊባትና ድንግል የሆነችውን የእኔንም ሴት ልጅ! አውጥቼ ልስጣችሁ፤ ተጠቀሙባቸው፤ የምትፈልጉትንም ነገር አድርጉባቸው፤ በዚህ ሰው ላይ ግን ክፉ ነገር አታድርጉ!” አላቸው።


ጧትም ጎሕ ሲቀድ ያቺ ሴት መጥታ ባልዋ ባደረበት በሽማግሌው ቤት በር አጠገብ ወደቀች፤ ፀሐይ እስክትወጣም ድረስ በዚያ ነበረች፤


የጊብዓ ሰዎች በእኔ ላይ አደጋ ለመጣል መጥተው በሌሊት ቤቱን ከበቡት፤ በመጀመሪያ እኔን ለመግደል አስበው ነበር፤ በኋላ ግን በቊባቴ ላይ ተረባርበው ስላመነዘሩባት ሞተች፤


跟着我们:

广告


广告