Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሽማግሌውም በከተማይቱ አደባባይ የተቀመጠውን ሰው አይቶ “ከየት መጣህ? የምትሄደውስ ወዴት ነው?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሽማግሌው ቀና ብሎ መንገደኛውን በከተማዪቱ አደባባይ ላይ ባየው ጊዜ፣ “ከወዴት መጣህ? ወዴትስ ትሄዳለህ?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሽማግሌው ቀና ብሎ መንገደኛውን በከተማይቱ አደባባይ ላይ ባየው ጊዜ፥ “ከወዴት መጣህ? ወዴትስ ትሄዳለህ?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዐይ​ኑ​ንም አን​ሥቶ መን​ገ​ደ​ኛ​ውን በከ​ተ​ማው አደ​ባ​ባይ አየ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ውም፥ “ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ? ከወ​ዴ​ትስ መጣህ?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዓይኑንም አንሥቶ መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየ፥ ሽማግሌውም፦ ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ? አለው።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:17
7 交叉引用  

መልአኩም “የሣራይ አገልጋይ አጋር ሆይ፥ ከወዴት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጂአለሽ?” አላት። እርስዋም “እኔ ከእመቤቴ ከሣራይ ሸሽቼ ነው” አለችው።


የመጀመሪያዎቹንም እረኞች እንዲህ በማለት አዘዛቸው፤ “ወንድሜ ዔሳው በመንገድ አግኝቶ ‘የማን ሰዎች ናችሁ? ወዴትስ ትሄዳላችሁ? እነዚህ የምትነዱአቸው ከብቶች የማን ናቸው?’ ብሎ የጠየቃችሁ እንደ ሆነ፥


አንድ ቀን ወደ ሀብታሙ ሰው ቤት አንድ መንገደኛ መጣ፤ ሀብታሙ ሰው ለእንግዳው የሚሆን ምግብ ለማዘጋጀት ከእንሰሶቹ አንዱን ማረድ አልፈለገም፤ ይህንንም በማድረግ ፈንታ የድኻውን ሰው ግልገል ወስዶ በማረድ ለእንግዳው ምግብ አዘጋጀ።”


አውራ ጐዳናዎች ባዶ ሆኑ፤ በመንገዶቹ ላይ ተጓዦች የሉም፤ ቃል ኪዳን ፈረሰ፤ የውል ስምምነቶች ተጥሰዋል፤ ከዚህም የተነሣ ምክር የሚሰጠው ሰው አልተገኘም።


የእስራኤል ተስፋ አንተ ብቻ ነህ፤ ከመቅሠፍት የምታድነንም አንተ ነህ፤ ታዲያ በምድራችን እንደ እንግዳ፥ ለአንድ ቀን እንደሚያድር መንገደኛስ የሆንከው ለምንድን ነው?


በዚያም ተቀምጠው ሳሉ በእርሻ ቦታ የቀን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ቤቱ የሚመለስ አንድ ሽማግሌ በአጠገባቸው አለፈ፤ ይህ ሰው አስቀድሞ ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር የመጣ ሲሆን፥ አሁን ግን የሚኖረው በጊብዓ ነበር፤ በዚያ የሚኖሩት ሌሎቹ ሰዎች ግን ከብንያም ነገድ የተወለዱ ናቸው፤


ሌዋዊውም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም ነበርን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤትና በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ቤታችን ለመድረስ በጒዞ ላይ ነን፤ ወደ ቤቱ ወስዶ የሚያሳድረን እስከ አሁን አላገኘንም፤


跟着我们:

广告


广告