Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በዚያም ተቀምጠው ሳሉ በእርሻ ቦታ የቀን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ቤቱ የሚመለስ አንድ ሽማግሌ በአጠገባቸው አለፈ፤ ይህ ሰው አስቀድሞ ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር የመጣ ሲሆን፥ አሁን ግን የሚኖረው በጊብዓ ነበር፤ በዚያ የሚኖሩት ሌሎቹ ሰዎች ግን ከብንያም ነገድ የተወለዱ ናቸው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በዚያች ምሽት ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር መጥቶ በጊብዓ የሚኖር አንድ መጻተኛ ሽማግሌ ከዕርሻ ሥራው መጣ፤ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በዚያች ምሽት ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር መጥቶ በጊብዓ የሚኖር አንድ መጻተኛ ሽማግሌ ከዕርሻ ሥራው መጣ፤ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነሆም፥ አንድ ሽማግሌ ከእርሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፥ ይህም ሰው ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ነበረ በጊብዓም በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፥ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:16
16 交叉引用  

ወደ መጣህበት ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ፥ እንጀራህን በግንባርህ ላብ ትበላለህ።” ዐፈር ነህና፥ ወደ ዐፈርም ትመለሳለህ።


ከዚህ በኋላ ሰዎች ለሥራ ይሰማራሉ፤ እስከሚመሽም ድረስ ሲሠሩ ይውላሉ።


ሠርተህ የምታፈራውን ትመገባለህ፤ ደስታና ሀብትም ታገኛለህ።


ያለ ድካም በቀላሉ የተገኘ ሀብት ወዲያው ይጠፋል፤ ተግቶ በመሥራት የተገኘ ሀብት ግን እየበዛ ይሄዳል።


ተግቶ መሥራት ጥቅምን ያስገኛል፤ ወሬኛነት ግን ያደኸያል።


በመጀመሪያ በርስትህ ላይ ለኑሮህ የሚያስፈልግህን ሁሉ አደራጅ፤ ከዚያ በኋላ ቤት ሥራ።


ታዲያ፥ በዚህ ዓለም የተደረጉትን ነገሮች ሁሉ በጥበብ መርምሬ ለማጥናት ወሰንኩ፤ ይህችን ከባድ ጭነት የሰው ልጆች ይደክሙበት ዘንድ እግዚአብሔር ሰጥቶአቸዋል።


የጉልበት ሥራ የሚሠራ ሰው ብዙም ሆነ ጥቂት ቢመገብ የሰላም እንቅልፍ አግኝቶ ያድራል፤ የባለ ጸጋ ሰው የሀብት ብዛት ግን ሀብቱ እንቅልፍ ይነሣዋል።


የእስራኤል ሕዝብ በገባዖን ዘመን እንደ ነበሩት ሰዎች በጣም ረክሰዋል፤ እግዚአብሔርም በደላቸውን አስቦ ስለ ኃጢአታቸው ይቀጣቸዋል።


ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ ወዲያ አይስረቅ፤ ይልቅስ ለችግረኞች ይሰጥ ዘንድ ገንዘብ እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካም ነገርን ይሥራ።


ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ሊሠራ የማይፈልግ አይብላ” የሚል ደንብ ሰጥተናችሁ ነበር።


በእስራኤል ገና ንጉሥ ባልነበረበት ጊዜ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ራቅ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚኖር አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ይህ ሰው በይሁዳ ግዛት ከምትገኘው ከቤተልሔም አንዲት ልጃገረድ ቊባት ወስዶ ነበር፤


ስለዚህ ኢየሩሳሌምን አልፈው ጒዞአቸውን ወደፊት ቀጠሉ፤ በብንያም ግዛት በምትገኘው በጊብዓ ሲደርሱ ፀሐይ ጠለቀች፤


የሚያድሩበትንም ስፍራ ፈልገው ለማግኘት ከመንገድ ወጣ አሉ፤ ወደ ከተማይቱም ገብተው በአደባባዩ አጠገብ ተቀመጡ፤ ነገር ግን ወደ ቤት ወስዶ የሚያሳድራቸው ማንንም አላገኙም።


ሽማግሌውም በከተማይቱ አደባባይ የተቀመጠውን ሰው አይቶ “ከየት መጣህ? የምትሄደውስ ወዴት ነው?” ሲል ጠየቀው።


跟着我们:

广告


广告