Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 18:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እነርሱም ወጥተው በይሁዳ በምትገኘው ከቂርያትይዓሪም በስተ ምዕራብ ሰፈሩ፤ ያ ስፍራ እስከ አሁን የዳን ሰፈር ተብሎ የሚጠራውም ስለዚህ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ወጥተውም በይሁዳ ምድር ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ እንግዲህ ከቂርያትይዓይሪም በስተ ምዕራብ ያለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር መባሉ ከዚሁ የተነሣ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ወጥተውም በይሁዳ ምድር ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ እንግዲህ ከቂርያትይዓሪም በስተ ምዕራብ ያለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር መባሉ ከዚህ የተነሣ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ወጥ​ተ​ውም በይ​ሁዳ ቂር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰፈሩ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፤ እነ​ሆም፥ ቦታዉ ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም በስ​ተ​ኋላ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ወጥተውም በይሁዳ ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፥ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፥ እነሆም፥ ከቂርያትይዓሪም በስተ ኋላ ነው።

参见章节 复制




መሳፍንት 18:12
10 交叉引用  

የቃል ኪዳኑ ታቦት ግን ንጉሥ ዳዊት ከቂርያትይዓሪም ባመጣው ጊዜ በኢየሩሳሌም አዘጋጅቶለት በነበረው ድንኳን ውስጥ ይገኝ ነበር።


ደግሞም ቂርያትባዓል ወይም ቂርያትይዓሪምና ራባ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው ያሉትን ትናንሽ ከተሞችን ይጨምራሉ።


ከዚያም ድንበሩ ከተራራው ጫፍ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ምንጮች ይደርሳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ይወጣል፤ ወደ ባዓላ ወይም ቂርያት ይዓሪም ይታጠፋል፤


ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጒዞ ጀምረው ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሕዝብ ወደሚኖሩባቸው ከተሞች ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ በኤሮትና ቂርያትይዓሪም ተብለው ይጠሩ ነበር፤


በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ በነበረበት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ያበረታው ጀመር።


ስለዚህ ከዳን ነገድ የጦር መሣሪያ የታጠቁ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሡ፤


ከዚያም ጒዞአቸውን በመቀጠል በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ሚካ ቤት መጡ።


በቂርያትይዓሪም ወደሚኖሩትም ሕዝብ መልእክተኞችን ልከው “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኛ አምጥተዋታልና መጥታችሁ ውሰዱት” አሉ።


የቂርያትይዓሪም ሰዎችም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስደው በኮረብታ ላይ ወደሚኖረው አቢናዳብ ተብሎ ወደሚጠራ ሰው ቤት አስገቡት፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን የተለየ እንዲሆን አደረጉ።


跟着我们:

广告


广告