Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 17:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይህም ሰው የሚኖርበትን ስፍራ ለማግኘት ከቤተልሔም ተነሥቶ ሄደ፤ በጒዞም ላይ ሳለ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ሚካ ቤት መጣ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ይህም ሰው ሌላ መኖሪያ ስፍራ ለመፈለግ ከይሁዳ ቤተ ልሔም ለቅቆ ሄደ። በሚጓዝበትም ጊዜ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳለው ወደ ሚካ ቤት መጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ይህም ሰው ሌላ መኖሪያ ስፍራ ለመፈለግ ከተማይቱን ለቆ ሄደ። በሚጓዘበትም ጊዜ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳለው ወደ ሚካ ቤት መጣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ይህም ሰው በአ​ገ​ኘው ስፍራ ይኖር ዘንድ ከይ​ሁዳ ከተማ ከቤተ ልሔም ሄደ፤ በዚ​ያም ያድር ዘንድ ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት ደረሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ይህም ሰው የሚቀመጥበትን ስፍራ ለመሻት ከከተማው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ወጣ፥ ሲሔድም ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጣ።

参见章节 复制




መሳፍንት 17:8
6 交叉引用  

የአሮን ልጅ አልዓዛርም ሞተ፤ በጊብዓም ተቀበረ፤ እርስዋም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኝና ለልጁ ለፊንሐስ መኖሪያ የተሰጠች ትንሽ ከተማ ናት።


ወጣቱ ሌዋዊም ከሚካ ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ያም ወጣት ካህን ለሚካ እንደ ልጅ ሆነለት፤


በዚያን ወቅት በይሁዳ ግዛት በቤተልሔም ከተማ የሚኖር አንድ ወጣት ሌዋዊ ነበር፤


ሚካም “ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም “እኔ በይሁዳ ግዛት ከምትገኘው ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የምኖርበትን ስፍራ እየፈለግሁ ነው” ሲል መለሰለት።


በእስራኤል አገር መሳፍንት ይገዙ በነበረበት ዘመን በሀገሩ ላይ ረሀብ ሆነ፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ክፍለ ሀገር ከቤተልሔም አንድ ሰው ከሚስቱና ከሁለት ወንዶች ልጆቹ ጋር ለመኖር ወደ ሞአብ አገር ሄደ።


跟着我们:

广告


广告