Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከዚያም በኋላ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው፤ እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ “እንደ ወትሮው በጣጥሼ እሄዳለሁ” ብሎ አሰበ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተለየው አላወቀም ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እርሷም፣ “ሳምሶን፤ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቅቶ፣ “እንደ ወትሮው አደርጋለሁ” አለ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ተወው አላወቀም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እርሷም፥ “ሳምሶን፤ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቅቶ፥ “እንደ ወትሮው አደርጋለሁ” አለ፤ ነገር ግን ጌታ እንደ ተወው አላወቀም ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ደሊ​ላም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም ነቅቶ፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወት​ሮ​ውም ጊዜ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም” አለ። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ እንደ ተለ​የው አላ​ወ​ቀም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ከእንቅልፉም ነቅቶ፦ እወጣለሁ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ተለየው አላወቀም።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:20
21 交叉引用  

ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤


የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን ለዘራፊና ለቀማኛ አሳልፎ የሰጠ ማነው? ይህን ያደረገው እግዚአብሔር ራሱ አይደለምን? ይህም የሆነው እኛ ስለ በደልነው፥ በሚፈቅደው መንገድ ስላልሄድንና ለሕጉም ታዛዦች ስላልሆንን ነው።


ባዕዳን ጒልበታቸውን በዘበዙት፤ እነርሱ ግን አልተገነዘቡትም፤ ሽበት ጣል ጣል አድርጎባቸዋል፤ እነርሱ ግን አልተገነዘቡትም።


ስለዚህ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እዚያም የሚኖሩትን ሕዝቦች አትፍሩአቸው፤ እኛ በቀላሉ በጦርነት ድል እንነሣቸዋለን፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፎአል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።”


ወደ ደቀ መዛሙርትህም አምጥቼው ነበር፤ ነገር ግን ሊፈውሱት አልቻሉም።”


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እምነታችሁ ጐደሎ ስለ ሆነ ነው፤ በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወዲያ ሂድ!’ ብትሉት ይሄዳል፤ የሚሳናችሁም ምንም ነገር አይኖርም።


አገልግሎታችንን መፈጸም እንድንችል ብቁ የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው እንጂ እኛስ በገዛ ራሳችን ምንም ለማድረግ ብቁ አይደለንም።


ፈጣሪአቸው አሳልፎ ካልሰጣቸውና አምላካቸውም ካልተዋቸው በቀር እንዴት አንዱ ሺሁን ያሳድዳል? ወይም ሁለቱ ዐሥር ሺሁን ያባርራሉ?


እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን መቋቋም ያልቻሉበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እነርሱ ራሳቸው እንዲጠፉ ስለ ተፈረደባቸው ከጠላቶች ፊት ወደ ኋላ ይሸሻሉ። እንዲደመሰስ የታዘዘውን ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ እኔ ከእናንተ ጋር አልሆንም።


ከዚህ በኋላ ደሊላ ተኝቶ ሳለ የራሱን ጠጒር ሰባቱን ቁንዳላዎች ከድር ጋር ጐንጒና በችካል ቸከለችው፤ ከዚያ በኋላ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” ብላ ጮኸች፤ እርሱ ግን ከእንቅልፉ ነቅቶ ጠጒሩን ከችካሉና ከድሩ ላይ ነቀለው።


ደሊላ ሶምሶንን በጭንዋ ላይ አስተኝታ፤ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገች። አንድ ሰውም ጠርታ ሰባቱን የጠጒሩን ቁንዳላዎች እንዲቈረጡ አደረገች፤ ኀይሉም ከእርሱ ተለይቶት ስለ ነበር በማዋረድ ታስጨንቀው ነበር፤


ፍልስጥኤማውያንም ከማረኩት በኋላ ሁለቱን ዐይኖቹን አወጡ፤ ወደ ጋዛም ወስደው በነሐስ ሰንሰለት በማሰር በታሰረበት ቤት እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤


ነገር ግን ሶምሶን ከሴቲቱ ጋር ተኝቶ የቈየው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ከዚያን በኋላ ከመኝታው ተነሣ፤ የከተማይቱን ቅጽር በር፥ ሁለቱን ምሶሶዎችና መቈለፊያዎቹን ሁሉ ፈነቃቀለ፤ ያንን ሁሉ በትከሻው ተሸክሞ ከኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኮረብታ ድረስ ወሰደ።


በሌላ ክፍል ሆነው የሚጠባበቁ ወንዶች ስለ ነበሩ እርሷ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” ስትል ጮኸች፤ እርሱ ግን ፈትል እሳት ሲነካው እንደሚበጣጠስ ጠፍሮቹን በጣጠሳቸው፤ ስለዚህ አሁንም ብርታት የሚያገኝበትን ምሥጢር ገና አልደረሱበትም ነበር።


የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ስለ ተለየ ከእግዚአብሔር የተላከ ክፉ መንፈስ ያሠቃየው ነበር፤


በማግስቱም በድንገት ከእግዚአብሔር የተላከ ክፉ መንፈስ ሳኦልን ተቈራኘው፤ በቤቱም ውስጥ እንደ እብድ ይለፈልፍ ነበር፤ ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ በነበረው ዐይነት ለሳኦል በገና ይደረድርለት ነበር፤ ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።


እግዚአብሔር እርሱን ትቶ ከዳዊት ጋር ስለ ነበረ ሳኦል ዳዊትን ፈራው፤


跟着我们:

广告


广告