Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ደሊላም ሶምሶንን “እስከ አሁን ድረስ አሞኘኸኝ፤ እውነቱንም አልነገርከኝም፤ አሁንም አንተን እንዴት ማሰር እንደሚቻል እባክህ ንገረኝ” አለችው። እርሱም “የራሴን ጠጒር ሰባቱን ቁንዳላዎች ከድር ጋር ብትጐነጒኚው፥ በችካልም ብትቸክዪው እንደማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ደግሞም ደሊላ ሳምሶንን፣ “እስካሁን አሞኝተኸኛል፤ ዋሽተኸኛል። እባክህን አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደ ሆነ ንገረኝ” አለችው። እርሱም መልሶ፣ “የራስ ጠጕሬን ሰባት ሹሩባዎች ከድር ጋራ ጐንጕነሽ በችካል ብትቸክዪው፣ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። ደሊላም መተኛቱን አይታ ሰባቱን ሹሩባዎቹን ከድር ጋራ ጐነጐነችው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ደግሞም ደሊላ ሳምሶንን፥ “እስካሁን አሞኝተኸኛል፤ ዋሽተኸኛል። እባክህን አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ” አለችው። እርሱም መልሶ፥ “የራስ ጠጉሬን ሰባት ቈንዳላዎች ከድር ጋር ጐንጉነሽ በችካል ብትቸክይው፥ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “እስከ አሁን ድረስ አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝም ሐሰት ነው፤ የም​ት​ታ​ሰ​ር​በት ምን እን​ደ​ሆነ ንገ​ረኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “የራ​ሴን ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ብት​ጐ​ነ​ጕ​ኚው፥ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ብት​ቸ​ክ​ዪው፥ ከሰ​ዎች እንደ አንዱ እደ​ክ​ማ​ለሁ፥” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ደሊላም ሶምሶንን፦ እስከ አሁን ድረስ አታለልኸኝ፥ የነገርኸኝም ሐሰት ነው፥ የምትታሰርበት ምን እንደ ሆነ ንገረኝ አለችው። እርሱም፦ የራሴን ጠጉር ሰባቱን ጉንጉን ከድር ጋር ብትጐነጉኚው፥ በችካልም ብትቸክዪው፥ እደክማለሁ፥ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ አላት።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:13
4 交叉引用  

ከዚህም የተነሣ እርስዋ በሠርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ አለቀሰች፤ አጥብቃም ስለ ነዘነዘችው የእንቆቅልሹን ፍች በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርስዋም ሄዳ ለፍልስጥኤማውያኑ ነገረቻቸው።


ደሊላም ሶምሶንን “እነሆ! አታለልከኝ፤ እውነቱንም አልነገርከኝም፤ አሁንም አንተን እንዴት ማሰር እንደሚቻል እባክህ ንገረኝ!” አለችው።


ደሊላም አዲስ ገመድ ወስዳ አሰረችው፤ በሌላ ክፍል ሆነው የሚጠባበቁ ወንዶች ስለ ነበሩ እርሷ “ሶምሶን፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” ስትል ጮኸች፤ እርሱ ግን ገመዱን ከክንዱ እንደ ፈትል በጣጠሰው።


ከዚህ በኋላ ደሊላ ተኝቶ ሳለ የራሱን ጠጒር ሰባቱን ቁንዳላዎች ከድር ጋር ጐንጒና በችካል ቸከለችው፤ ከዚያ በኋላ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” ብላ ጮኸች፤ እርሱ ግን ከእንቅልፉ ነቅቶ ጠጒሩን ከችካሉና ከድሩ ላይ ነቀለው።


跟着我们:

广告


广告