Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 14:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የእግዚአብሔርም መንፈስ ለእርሱ ብርታትን ሰጠው፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ውብ የሆነውንም ልብሳቸውን ሁሉ በመግፈፍ አምጥቶ የእንቆቅልሹን ፍች ላወቁት ሰዎች ሰጣቸው። በሆነውም ነገር ሁሉ እጅግ ተቈጥቶ ወደ ቤተሰቦቹ ተመለሰ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከዚያም የእግዚአብሔር መንፈስ በሳምሶን ላይ በኀይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቍጣ እንደ ነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከዚያም የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቁጣ እንደነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስ​ቀ​ሎ​ናም ወረደ፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ገፍፎ እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን ለነ​ገ​ሩት ሰዎች ሰጠ። ሶም​ሶ​ንም ተቈጣ፤ ወደ አባ​ቱም ቤት ተመ​ለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ በኃይል ወረደ፥ ወደ አስቀሎናም ወረደ፥ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፥ ልብሳቸውንም ወስዶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጠ። ቁጣውም ነደደ፥ ወደ አባቱም ቤት ወጣ።

参见章节 复制




መሳፍንት 14:19
9 交叉引用  

የይሁዳም ነገድ ጋዛንና አስቀሎናን፥ አቃሮንንና አካባቢዎቻቸውን ያዙ።


በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ በነበረበት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ያበረታው ጀመር።


ስለዚህ በሰባተኛው ቀን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት፥ የከተማይቱ ሰዎች “ከማር የጣፈጠ፥ ከአንበሳስ የበረታ ምን አለ?” ሲሉ የእንቆቅልሹን ፍች ነገሩት። ሶምሶንም “በእኔ ጊደር ባታርሱ ኖሮ፥ መልሱን ማግኘት ባልቻላችሁም ነበር” አላቸው።


በድንገትም የእግዚአብሔር መንፈስ ሶምሶንን አበረታው፤ ስለዚህም አንበሳውን እንደ አንድ የፍየል ጠቦት ያኽል በመቊጠር ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጥሎ ጣለው፤ ያደረገውንም ነገር ለወላጆቹ አልነገራቸውም።


ሶምሶንም ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እየደነፉ መጡበት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አበረታው፤ ክንዱ የታሰሩበት ገመዶች እሳት እንደ ነካቸው የሐር ፈትል ከእጁ ላይ ቀልጠው ወደቁ።


የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሻን ፊሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሻን ሪሽዓታይምን ድል አደረገው።


ሳኦልም ይህን በሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኀይል ወረደ፤ የሳኦልም ቊጣ እጅግ ገነፈለ።


ስለ በደላቸው የሚከፈሉ ስጦታዎች ይሆኑ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ለእግዚአብሔር የላኩአቸው በእባጮች አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች አሽዶድ፥ ጋዛ፥ አስቀሎና፥ ጋትና ዔቅሮን ተብለው በሚጠሩት ከተሞቻቸው ስም የተላኩ ነበሩ፤


ሕዝቡም፥ “ስለ በደል የሚከፈል ይሆን ዘንድ ከምን ዐይነት ስጦታ ጋር እንላከው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “በእባጩ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጒልቻ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ብዛት በአይጥ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጉልቻ መሆን አለበት፤ በእናንተ ሁሉና በአምስቱ ገዢዎች ላይ የተላከው መቅሠፍት አንድ ዐይነት ነው።


跟着我们:

广告


广告