Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 14:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በአራተኛው ቀን የሶምሶንን ሚስት እንዲህ አሉአት፤ “ባልሽን አግባብተሽ የእንቆቅልሹን ፍች እንዲነግረን አድርጊ፤ ይህን ካላደረግሽ ግን የአባትሽን ቤት በእሳት አያይዘን አንቺንም በውስጡ በመጨመር እናቃጥልሻለን፤ ለካስ እናንተ ሁለታችሁም ወደ ግብዣችሁ የጠራችሁን ልትዘርፉን ኖሮአልን?”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በአራተኛው ቀን የሳምሶንን ሚስት፣ “የዕንቈቅልሹን ፍች እንዲነግረን ባልሽን እስኪ አግባቢልን፤ አለዚያ አንቺንም የአባትሽንም ቤተ ሰብ በእሳት እናቃጥላችኋለን፤ ጠርታችሁ የጋበዛችሁን ልትዘርፉን ነው?” አሏት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በአራተኛው ቀን የሳምሶንን ሚስት፥ “የእንቈቅልሹን ፍች እንዲነግረን ባልሽን እስቲ አግባቢልን፤ ያለዚያ አንቺንም የአባትሽንም ቤተሰብ በእሳት እናቃጥላችኋለን፤ ጠርታችሁ የጋበዛችሁን ልትዘርፉን ነው እንዴ?” አሏት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከዚህ በኋላ በአ​ራ​ተ​ኛው ቀን የሶ​ም​ሶ​ንን ሚስት፥ “እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን እን​ዲ​ነ​ግ​ርሽ ባል​ሽን አባ​ብ​ይው፤ አለ​ዚ​ያም አን​ቺ​ንና የአ​ባ​ት​ሽን ቤት በእ​ሳት እና​ቃ​ጥ​ላ​ለን፤ ወይስ ወደ​ዚህ የጠ​ራ​ች​ሁን ልታ​ደ​ኸ​ዩን ነውን?” አሉ​አት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በአራተኛውም ቀን የሶምሶንን ሚስት፦ እንቈቅልሹን እንዲነግረን ባልሽን ሸንግዪው፥ አለዚያም አንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፥ ወደዚህ ጠራችሁን ልትገፉን ነውን? አሉአት።

参见章节 复制




መሳፍንት 14:15
9 交叉引用  

ምናልባትም እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ከበደል ንጹሕ የሆነውን ሰው መንገድ ላይ አድብተን እንድንገድለው ከእኛ ጋር ና!


የአመንዝራ ሴት ከንፈር የማር ወለላ የሚያንጠባጥብ ይመስላል፤ ንግግርዋም ከዘይት ይልቅ የለዘበ ነው።


አንድ ወንድ ሴትኛ ዐዳሪዋን በአንድ እንጀራ ዋጋ ሊያገኛት ይችላል፤ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ማመንዘር ግን የሕይወት ዋጋ ያስከፍላል።


በሰው ላይ እምነትህን አትጣል፤ በቅርብ ወዳጅህም አትተማመን፤ አቅፈሃት ለምትተኛው ሚስትህ የምትናገረው ቃል እንኳ ጥንቃቄ የተሞላበት ይሁን።


የኤፍሬም ሰዎች ለጦርነት ተዘጋጅተው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ጻፎን በደረሱ ጊዜ ዮፍታሔን “ዐሞናውያንን ለመውጋት ወሰን አልፈህ ስትሄድ እኛን ያልጠራኸን ለምንድን ነው? እንግዲህ እኛም ቤትህን በላይህ እናቃጥለዋለን!” አሉት።


እርሱም “ከበላተኛው መብል ተገኘ፤ ከብርቱውም ጣፋጭ ነገር ወጣ” አላቸው። እስከ ሦስት ቀን ድረስ እንቆቅልሹን መፍታት አልቻሉም።


ፍልስጥኤማውያን ይህን ያደረገው ማን እንደሆን በጠየቁ ጊዜ፥ ሶምሶን መሆኑን ተረዱ፤ የቲምና ተወላጅ የሆነው ዐማቱ የሶምሶንን ሚስት ሚዜው ለነበረ ሌላ ሰው ሰጥቶበት ነበር፤ ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ሄደው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጠሉ።


የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ወደ እርስዋ ሄደው እንዲህ አሉአት፤ “ሶምሶንን አግባብተሽ ይህን ሁሉ ብርታት ያገኘው ከምን እንደ ሆነና እንዴትስ አስረን በቊጥጥራችን ሥር በማድረግ ልናሸንፈው እንደምንችል ጠይቂው፤ እያንዳንዳችንም አንድ ሺህ አንድ መቶ ጥሬ ብር እንሰጥሻለን።”


跟着我们:

广告


广告