Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 13:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ሚስቱ ግን “እግዚአብሔር ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ የሚቃጠል መሥዋዕታችንንና የእህል ቊርባናችንን ባልተቀበለም ነበር፤ ይህን ሁሉ አሁን ባላሳየንና እንዲህ ያለውን ነገር ሁሉ ባልነገረንም ነበር” ስትል መለሰችለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ሚስቱ ግን መልሳ እንዲህ አለችው፣ “እግዚአብሔር ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቍርባኑን ከእጃችን ባልተቀበለን፤ ደግሞም ይህን ነገር ሁሉ ባላሳየንና እንዲህ ያለውንም ነገር በዚህ ጊዜ ባልነገረን ነበር።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሚስቱ ግን መልሳ እንዲህ አለችው፥ “ጌታ ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፥ የሚቃጠለውን መሥዋትና የእህል ቁርባኑን ከእጃችን ባልተቀበለን፤ ደግሞም ይህን ነገር ሁሉ ባላሳየንና እንዲህ ያለውንም ነገር በዚህ ጊዜ ባልነገረን ነበር።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሚስ​ቱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ሊገ​ድ​ለን ቢወ​ድድ ኖሮ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ከእ​ጃ​ችን ባል​ተ​ቀ​በ​ለን፥ ይህ​ንም ነገር ሁሉ ባላ​ሳ​የን፥ እን​ዲህ ያለ ነገ​ርም በዚህ ጊዜ ባላ​ሰ​ማን ነበር” አለ​ችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ሚስቱም፦ እግዚአብሔርስ ሊገድለን ቢወድድ ኖሮ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ከእጃችን ባልተቀበለን፥ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን፥ እንዲህ ያለ ነገርም በዚህ ጊዜ ባላስታወቀን ነበር አለችው።

参见章节 复制




መሳፍንት 13:23
12 交叉引用  

የልብህን ምኞት ይስጥህ፤ ሐሳብህን ሁሉ ይፈጽምልህ፤


እግዚአብሔር ለሚታዘዙት ሁሉ ወዳጃቸው ነው፤ ለእነርሱ የገባውንም ቃል ኪዳን ያጸናል።


ሕያዋን በሚኖሩባት ምድር እስካለሁ ድረስ የእግዚአብሔርን በጎነት እንደማይ እተማመናለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ስለ ረዳኸኝና ስላጽናናኸኝ፥ ጠላቶቼ አይተው ያፍሩ ዘንድ፥ ለእኔ ሞገስን የመስጠት ምልክትህን አሳየኝ።


እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎችን ይጠላል፤ ልበ ቅኖችን ግን አጥብቆ ይወዳቸዋል።


እኔ በአብ እንዳለሁ፥ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፥ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “የሚወደኝ ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፤ እኛ ወደ እርሱ መጥተን ከእርሱ ጋር አብረን እንኖራለን።


አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጥኩላችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፤


ዐይን እጅን “አንተ አታስፈልገኝም!” ሊለው አይችልም፤ ራስም እግርን “አንተ አታስፈልገኝም!” ሊለው አይችልም፤


ሴቲቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሶምሶን ብላ ጠራችው፤ ልጁም አደገ፤ እግዚአብሔርም ባረከው፤


跟着我们:

广告


广告