Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 13:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ቀጥሎም ማኑሄ “የተናገርከው ቃል ሲፈጸም ለሚወለደው ልጅ ምን መደረግ አለበት?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ማኑሄም፣ “ያልኸው በሚፈጸምበት ጊዜ የልጁ ሕይወት የሚመራው እንዴት ነው? እኛስ ምን ማድረግ አለብን?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ማኑሄም፥ “ያልከው በሚፈጸምበት ጊዜ የልጁ ሕይወት የሚመራው እንዴት ነው? እኛስ ምን ማድረግ አለብን?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ማኑ​ሄም፥ “እነሆ፥ ቃልህ በደ​ረሰ ጊዜ የልጁ ነገሩ፥ ግብ​ሩስ ምን​ድን ነው?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ማኑሄም፦ ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድር ነው? የምናደርግለትስ ምንድር ነው? አለው።

参见章节 复制




መሳፍንት 13:12
7 交叉引用  

ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”


የምተማመነው በአንተ ስለ ሆነ በየጠዋቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ ሕይወቴን በዐደራ ለአንተ ስለ ሰጠሁ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።


ልጅን እንዴት መኖር እንደሚገባው ብታስተምረው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።


አባቴም እንዲህ እያለ ያስተምረኝ ነበር፤ “ቃሌን በሙሉ ልብህ ያዘው፤ ትእዛዞቼንም ፈጽም፤ በሕይወትም ትኖራለህ።


እናንተም ወላጆች ሆይ! በጌታ በኢየሱስ ሥነ ሥርዓትን በማስተማር፥ በማረምና በመገሠጽ አሳድጉአቸው እንጂ ልጆቻችሁን በማስቈጣት አታስመርሩአቸው።


ማኑሄም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሚስቱን ተከትሎ ሄደ፤ ወደ ሰውየውም ቀርቦ “ከሚስቴ ጋር ተነጋግረህ የነበርከው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም “አዎ! እኔ ነኝ” ሲል መለሰ።


መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰ፥ “ሚስትህ የነገርኳትን ሁሉ ነገር ለማድረግ ትኲረት መስጠት አለባት።


跟着我们:

广告


广告