መሳፍንት 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ኢብጻን ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ሴቶች ልጆቹን ከጐሣው ውጪ ከሆኑ ወንዶች ጋር አጋባቸው፤ እንዲሁም ከጐሣው ውጪ የሆኑ ሴቶች ልጆችን አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋር እንዲጋቡ አደረገ፤ ኢብጻን ሰባት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆነ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እርሱም ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት። ሴቶች ልጆቹንም ከጐሣው ውጭ ለሆኑ ሰዎች ዳራቸው፤ ከጐሣው ውጭ የሆኑ ሠላሳ ልጃገረዶች አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋራ አጋባቸው። ኢብጻን በእስራኤል ላይ ሰባት ዓመት ፈራጅ ሆነ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እርሱም ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት። ሴቶች ልጆቹንም ከጐሣው ውጭ ለሆኑ ሰዎች ዳራቸው፤ ጐሣው ውጭ የሆኑ ሠላሳ ልጃገረዶች አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋር አጋባቸው። ኢብጻን በእስራኤል ላይ ሰባት ዓመት ፈራጅ ሆነ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሠላሳ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ ሠላሳ ሴቶች ልጆቹንም ወደ ውጭ ሀገር ዳረ፤ ለወንዶች ልጆቹም ከውጭ ሀገር ሠላሳ ሴቶች ልጆችን አመጣ። እስራኤልንም ሰባት ዓመት ገዛ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ሠላሳም ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት፥ ሠላሳ ሴቶች ልጆቹንም ወደ ውጭ አገር ዳረ፥ ለወንዶች ልጆቹም ከውጭ አገር ሴቶች ልጆችን አመጣ። በእስራኤልም ላይ ሰባት ዓመት ፈረደ። 参见章节 |