Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 11:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 የእስራኤላውያን ወጣት ሴቶች ልጆች በየዓመቱ ለአራት ቀን ያኽል ከቤታቸው ርቀው እየሄዱ ለገለዓዳዊው ለዮፍታሔ ሴት ልጅ ማዘናቸውና ማልቀሳቸው የተለመደ ሆነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 የእስራኤል ወጣት ሴቶች የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ልጅ በማሰብ በየዓመቱ እየወጡ የአራት ቀን ሐዘን ያደርጉላታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 የእስራኤል ወጣት ሴቶች የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ልጅ በማሰብ በየዓመቱ እየወጡ የአራት ቀን ኀዘን ያደርጉላታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሴቶች ልጆች ለገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊዉ ለዮ​ፍ​ታሔ ልጅ በዓ​መት አራት ቀን ያለ​ቅ​ሱ​ላት ዘንድ በዓ​መት በዓ​መት ይሄዱ ነበር። ይህ​ችም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሥር​ዐት ሆነች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 የእስራኤልም ሴቶች ልጆች በዓመት በዓመቱ እየሄዱ የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ልጅ በዓመት አራት ቀን ሙሾ እንዲያወጡ በእስራኤል ዘንድ ልማድ ሆነ።

参见章节 复制




መሳፍንት 11:40
6 交叉引用  

ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በዓመት ሦስት ጊዜ ያቀርብ ነበር፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ለእግዚአብሔር ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህም ዐይነት የቤተ መቅደሱ ሥራ ተፈጸመ።


ነቢዩ ኤርምያስም ለንጉሥ ኢዮስያስ የለቅሶ ሙሾ አወጣለት፤ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች አልቃሾች ኢዮስያስን በማስታወስ፥ በሚያለቅሱበት ጊዜ በዚሁ በነቢዩ ኤርምያስ የለቅሶ ሙሾ ማልቀስ በእስራኤል አገር የተለመደ ሆነ፤ ይህም የለቅሶ ሙሾ የእስራኤልን የለቅሶ ሰቆቃ በያዘ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።


አይሁድ ለራሳቸው፥ ለዘሮቻቸው አይሁዳዊ መሆን ለሚፈልግ ሁሉ ቋሚ ደንብ አደረጉ፤ ይኸውም በየዓመቱ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ መርዶክዮስ በሰጠው መመሪያ መሠረት እነዚህ ሁለት ቀኖች ባለማቋረጥ ይከበራሉ።


ከሁለት ወር በኋላ ወደ አባትዋ ቤት ተመልሳ መጣች፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ቃል የገባውን ስለት ፈጸመባት፤ እርስዋም ወንድ ያላወቀች ድንግል ነበረች። ከዚያም ጊዜ አንሥቶ፥


የኤፍሬም ሰዎች ለጦርነት ተዘጋጅተው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ጻፎን በደረሱ ጊዜ ዮፍታሔን “ዐሞናውያንን ለመውጋት ወሰን አልፈህ ስትሄድ እኛን ያልጠራኸን ለምንድን ነው? እንግዲህ እኛም ቤትህን በላይህ እናቃጥለዋለን!” አሉት።


እነሆ አድምጡ! ውሃ በሚቀዳባቸው ጒድጓዶች ዙሪያ የሚሰማው የብዙ ሰዎች ድምፅ፥ የእግዚአብሔርን ድል ያበሥራል፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ድል አድራጊነት ይናገራል። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ፥ ከከተሞቻቸው ተሰልፈው ወረዱ።


跟着我们:

广告


广告