Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 11:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ዮፍታሔ በምጽጳ ወዳለው ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሴት ልጁ አታሞ ይዛ እየጨፈረች ልትቀበለው ወጣች፤ ያለ እርስዋም ሌላ ወንድ ወይም ሴት ልጅ አልነበረውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ዮፍታሔ ምጽጳ ወዳለው ቤቱ ተመለሰ። እነሆ፤ ልጁ አታሞ እየደለቀች በመዝፈን ልትቀበለው ወጣች፤ እርሷም አንዲት ልጁ ብቻ ነበረች፤ ከርሷ በቀር ወንድም ሆነ ሴት ልጅ አልነበረውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ዮፍታሔ ምጽጳ ወዳለው ቤቱ ተመለሰ፤ እነሆ፤ ልጁ አታሞ እየደለቀች በመዝፈን ልትቀበለው ወጣች፤ እርሷም አንዲት ልጁ ብቻ ነበረች፤ ከእርሷ በቀር ወንድም ሆነ ሴት ልጅ አልነበረውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ዮፍ​ታ​ሔም ወደ መሴፋ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ልጁ ከበሮ ይዛ እየ​ዘ​ፈ​ነች ልት​ቀ​በ​ለው ወጣች፤ ለእ​ር​ሱም የሚ​ወ​ድ​ዳት አን​ዲት ብቻ ነበ​ረች። ከእ​ር​ስ​ዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አል​ነ​በ​ረ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ዮፍታሄም ወደ ቤቱ ወደ ምጽጳ መጣ፥ እነሆም ልጁ ከበሮ ይዛ እየዘፈነች ልትገናኘው ወጣች፥ ለእርሱም አንዲት ብቻ ነበረች፥ ከእርስዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አልነበረውም።

参见章节 复制




መሳፍንት 11:34
18 交叉引用  

ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ሽርጥ በወገቡ ዙሪያ ታጥቆ እግዚአብሔርን በማክበር በሙሉ ኀይሉ ያሸበሽብ ነበር፤


በከበሮና በማሸብሸብ አመስግኑት፤ በክራርና በዋሽንት አመስግኑት።


ዘማሪዎች ከፊት፥ ሙዚቀኞች ከኋላ፥ አታሞ የሚመቱ ልጃገረዶች ከመካከል፥ ሆነው ይታያሉ።


የአሮን እኅት ነቢይቱ ማርያም ከበሮዋን አነሣች፤ ሌሎችም ሴቶች ከበሮዎቻቸውን እየመቱና እየጨፈሩ ይከተሉአት ጀመር፤


ልጃገረዶቻቸውም በደስታ ይጨፍራሉ፤ ወንዶች ወጣቶችና ሽማግሌዎችም ደስ ይላቸዋል፤ አጽናናቸዋለሁ፤ ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፥ ሐዘናቸውንም ወደ ሐሴት እለውጣለሁ፤


ሕዝቤ እስራኤል ሆይ፥ እንደገና ትገነባላችሁ፤ ትገነቢአለሽም፥ እንደገና ከበሮ ትይዢአለሽ፤ ከሚደሰቱት ጋር አብረሽ በመውጣት ትጨፍሪአለሽ።


“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።


ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በር አጠገብ ሲደርስ እነሆ፥ ሰዎች ሬሳ ተሸክመው ከከተማይቱ ይወጡ ነበር፤ የሞተው ሰው ለእናቱ አንድ ነበር፤ እናቱም ባልዋ የሞተባት መበለት ነበረች፤ ከከተማይቱም ብዙ ሰዎች ተከትለዋት ነበር።


ይህንንም ያለው ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆናት አንድያ ልጁ ታማ በሞት አፋፍ ላይ ስለ ነበረች ነው። ኢየሱስም ከእርሱ ጋር አብሮ ሲሄድ ሳለ ተከትለውት የነበሩ ብዙ ሰዎች በመጨናነቅ ይጋፉ ነበር።


ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጮኸ! “መምህር ሆይ፥ ይህ ለኔ አንድ ልጅ ነውና እንድታድንልኝ እለምንሃለሁ፤


ምጽጳ፥ ከፊራ፥ ሞጻ፥


ከዚህ በኋላ የዐሞናውያን ሠራዊት ለጦርነት ተዘጋጅቶ በገለዓድ ሰፈረ፤ የእስራኤልም ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው በገለዓድ ምጽጳ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሰፈሩ፤


ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ መሪዎች ጋር ሄደ። ሕዝቡም ገዢአቸውና መሪያቸው አደረጉት፤ ዮፍታሔም በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ጉዳይ መስማማቱን ገለጠ።


ከሰሜን እስከ ደቡብ፥ ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ እንዲሁም በስተምሥራቅ በገለዓድ ምድር ያሉት የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ በአንድነትም ሆነው በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ፤


ተጠባበቁ፤ በበዓሉ ዕለት የሴሎ ልጃገረዶች ለመጨፈር ሲመጡ እናንተም ከወይኑ ተክል ውስጥ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁ ከእነዚያ ልጃገረዶች መካከል እየጠለፋችሁ ሚስት አድርጋችሁ ውሰዱ፤ ወደ ብንያም ግዛትም ይዛችኋቸው ሂዱ።


跟着我们:

广告


广告