Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 1:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የይሁዳም ነገድ ጋዛንና አስቀሎናን፥ አቃሮንንና አካባቢዎቻቸውን ያዙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ደግሞም የይሁዳ ሰዎች ጋዛ፣ አስቀሎና፣ አቃሮን የተባሉትን ከተሞች ከነግዛቶቻቸው ያዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ደግሞም የይሁዳ ሰዎች ጋዛን ከነግዛቶቿ፥ አስቀሎን ከነግዛቶቿ፥ አቃሮን ከነግዛቶቿ ያዙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ይሁ​ዳም ጋዛ​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አስ​ቀ​ሎ​ና​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አቃ​ሮ​ን​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አዛ​ጦ​ን​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን አል​ወ​ረ​ሳ​ትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ይሁዳም ጋዛንና ዳርቻዋን፥ አስቀሎናንና ዳርቻዋን፥ አቃሮንንና ዳርቻዋን ያዘ።

参见章节 复制




መሳፍንት 1:18
14 交叉引用  

ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለውን ምድር ሁሉ ከቲፍሳሕ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታት ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጐረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር።


የምድርህንም ወሰን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳው እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ እንዲሰፋ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁ፤ ከፊትህም ታሳድዳቸዋለህ።


የጋዛ ሕዝብ በሐዘን ጠጒራቸውን ይላጫሉ፤ የአስቀሎና ሕዝብ ሁሉ ጸጥ እንዲሉ ይደረጋሉ። በፍልስጥኤም ሸለቆ ከጥፋት የተረፉትስ ሰውነታቸውን እየቈራረጡ የሚያዝኑት እስከ መቼ ነው?


ቀርጤስ ተብላ ከምትጠራ ደሴት የመጡ ሕዝቦች በጋዛ አካባቢ የሚኖሩ ኤዋውያን ተብለው የሚጠሩ ነዋሪዎችን ደምስሰው በእነርሱ ቦታ ሰፈሩ።]


ከዐናቅ ዘሮች በእስራኤል ምድር የተረፈ አልነበረም፤ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ በጋዛ፥ በጋትና በአሽዶድ ይኖሩ ነበር።


እነዚህም ከግብጽ በስተ ምሥራቅ ካለው ከሺሆን ወንዝ ጀምሮ ወደ ሰሜን እስከ ኤክሮን ድንበር ድረስ ያለው ነው። ይህም በአጠቃላይ ከነዓን ተብሎ ይጠራል። እርሱም የአምስቱ የፍልስጥኤም ማለት የጋዛ፥ የአሽዶድ፥ የአስቀሎና፥ የጋትና የኤክሮን ነገሥታት ግዛት ነው። ሌሎች ያልተያዙ ደግሞ በደቡብ በኩል ያለው የአቢብ ግዛት ነው።


ይኸው ድንበር በዔቅሮን ሰሜናዊ ኮረብታ ከፍ በማለት ወደ ሺከሮን አቅጣጫ ይታጠፍና የባዓላን ኮረብታና እንዲሁም ያብኒኤልን አልፎ ይሄዳል፤ መጨረሻውም የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤


የእግዚአብሔርም መንፈስ ለእርሱ ብርታትን ሰጠው፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ውብ የሆነውንም ልብሳቸውን ሁሉ በመግፈፍ አምጥቶ የእንቆቅልሹን ፍች ላወቁት ሰዎች ሰጣቸው። በሆነውም ነገር ሁሉ እጅግ ተቈጥቶ ወደ ቤተሰቦቹ ተመለሰ፤


ፍልስጥኤማውያንም ከማረኩት በኋላ ሁለቱን ዐይኖቹን አወጡ፤ ወደ ጋዛም ወስደው በነሐስ ሰንሰለት በማሰር በታሰረበት ቤት እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤


በምድሪቱ ላይ የቀሩትም፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መሪዎች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከባዓልሔርሞን ተራራ አንሥቶ እስከ ሐማት ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች የሚኖሩት ሒዋውያን ነበሩ።


ስለ በደላቸው የሚከፈሉ ስጦታዎች ይሆኑ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ለእግዚአብሔር የላኩአቸው በእባጮች አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች አሽዶድ፥ ጋዛ፥ አስቀሎና፥ ጋትና ዔቅሮን ተብለው በሚጠሩት ከተሞቻቸው ስም የተላኩ ነበሩ፤


跟着我们:

广告


广告