Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ይሁዳ 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ ትውልድ የሆነው ሔኖክ ሲናገር እንዲህ ብሎአል፦ “እነሆ እግዚአብሔር እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክቱ ጋር ሆኖ በሁሉም ላይ ለመፍረድ ይመጣል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነው ሔኖክ ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ሲል ተንብዮአል፤ “እነሆ፤ ጌታ ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳኑ ጋራ ይመጣል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነው ሄኖክ እንደነዚህ ላሉት እንዲህ ብሎ ተንብዮአል፦ “እነሆ ጌታ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቷል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14-15 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ “እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኀጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኀጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዐመፀኞችም ኀጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል፤” ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14-15 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ፦ እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።

参见章节 复制




ይሁዳ 1:14
18 交叉引用  

ያሬድ 162 ዓመት ሲሆነው ሔኖክን ወለደ፤


በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም።


እናንተም ተራራውን በሁለት ከፍሎ እስከ አጻል በደረሰው በዚህ ሸለቆ ውስጥ አልፋችሁ ታመልጣላችሁ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ምድር በተናወጠች ጊዜ የቀድሞ አባቶቻችሁ በሸሹት ዐይነት ትሸሻላችሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬም ቅዱሳኑን አስከትሎ ይመጣል።


የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ሆኖ ከመላእክቱ ጋር ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል።


“የሰው ልጅ በመላእክቱ ሁሉ ታጅቦ በክብር ሲመጣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል፤


ሙሴም እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጣ፤ ከኤዶም ላይ እንደ ንጋት ፀሐይ አበራ፤ ከፋራንም ተራራ ላይ አንጸባረቀ፤ በስተቀኙ የእሳት ነበልባል ነበር፤ ከእርሱም ጋር አእላፍ መላእክት ነበሩ።


በዚህ ዐይነት ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚመጣበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁ ነቀፋ የሌለበትና ቅዱስ እንዲሆን ያበረታችኋል።


እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ ቀርባችኋል፤ እርስዋ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ናት፤ በደስታ ወደተሰበሰቡት፥ በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት መላእክት ቀርባችኋል።


እነሆ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ሰው ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤ ይህ ነገር እውነት ነው፤ አሜን።


ወደዚያም ስመለከት በዙፋኑና በእንስሶቹ በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ብዛታቸውም በብዙ ሺህና በብዙ ሚሊዮን የሚቈጠር ነበር፤


跟着我们:

广告


广告