Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 7:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ለኢያሱ ከዚህ የሚከተለውን ማስረጃ አቀረቡለት፦ “እነርሱ ጥቂቶች ስለ ሆኑ በዐይ ላይ አደጋ ለመጣል ያለውን ሰው ሁሉ በአጠቃላይ ማዝመት አያስፈልግም፤ ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ሰዎች ብቻ ላክ፤ በዚያ ለመዋጋት መላውን ሠራዊት አትላክ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ወደ ኢያሱም ተመልሰው፣ “ጋይን ለመውጋት ሕዝቡ ሁሉ መሄድ አያስፈልገውም፤ በዚያ ያለው ሕዝብ ጥቂት ስለ ሆነ፣ ከተማዪቱን ለመውጋት ሁለት ወይም ሦስት ሺሕ ሰው ስለሚበቃ ሕዝቡ ሁሉ ወደዚያ በመሄድ አይድከም” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወደ ኢያሱም ተመልሰው እንዲህ አሉት፦ “ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይውጣ፤ ጥቂቶች ናቸውና ሕዝቡ ሁሉ ወደዚያ ለመሄድ አይድከም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወደ ኢያ​ሱም ተመ​ል​ሰው፥ “ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥ​ተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይ​ውጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ​ዚያ አት​ው​ሰድ፤ ጥቂ​ቶች ናቸ​ውና” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወደ ኢያሱም ተመልሰው፦ ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይውጣ፥ ጥቂቶች ናቸውና ሕዝቡ ሁሉ ወደዚያ ለመሄድ አይድከም አሉት።

参见章节 复制




ኢያሱ 7:3
9 交叉引用  

ሰነፍ አንድ ነገር ለማግኘት አጥብቆ ይመኛል፤ ይሁን እንጂ አያገኝም፤ ትጉህ ሠራተኛ ግን የሚፈልገውን ሁሉ ያገኛል።


መሥራት የማይፈልግ ሰነፍ ሰው ራሱን የገደለ ያኽል ይቈጠራል።


“በጠባብዋ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ በዚህች በር መግባት የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን መግባት አይችሉም እላችኋለሁ።


ስለዚህ ማንም የእነዚያን ሰዎች አለመታዘዝ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደ እግዚአብሔር የዕረፍት ቦታ ለመግባት እንትጋ።


ኢያሱ በኢያሪኮ ሳለ በቤትአዌን አጠገብ ከቤትኤል በስተምሥራቅ የምትገኘውን “ዐይ” ተብላ የምትጠራውን ከተማና የምድሪቱን አቀማመጥ አጥንተው ይመለሱ ዘንድ ጥቂት ሰዎችን ላከ። ይህንንም በትእዛዙ መሠረት ከፈጸሙ በኋላ፥


ስለዚህም ሦስት ሺህ እስራኤላውያን ዘምተው አደጋ ጣሉባት፤ ነገር ግን እነርሱ ከዐይ ወታደሮች ፊት ሸሹ፤


ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማረጋገጥ በይበልጥ የምትጓጉ ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም።


በዚህ ምክንያት የሚከተሉት ነገሮች እንዲጨመሩላችሁ ትጉ፦ በእምነት ላይ ደግነትን፥ በደግነት ላይ ዕውቀትን፥


跟着我们:

广告


广告