Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 20:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ለእስራኤል ሕዝብና በመካከላቸውም ለሚኖሩ መጻተኞች መማጸኛ ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ማንም ሰው በድንገተኛ አጋጣሚ ሰው ቢገድል፥ በሸንጎ ሳይፈረድበት እንዳይገደል ከእነዚያ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሄዶ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው እጅ ያመልጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሳያስበው በድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ወደ ተለዩት ከተሞች መሸሽ ይችላል፤ በማኅበሩ ፊት ከመቆሙ አስቀድሞም በደም ተበቃዩ መገደል የለበትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በማ​ኅ​በሩ ፊት እስ​ኪ​ቆ​ምና እስ​ኪ​መ​ረ​መር ድረስ ባለ​ደሙ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው ሳያ​ውቅ ሰውን የገ​ደለ ወደ​ዚያ እን​ዲ​ማ​ፀን፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ በመ​ካ​ካ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጥ መጻ​ተኛ የተ​መ​ረጡ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 20:9
5 交叉引用  

ስድስት ከተሞችን ምረጡ፤


እነርሱም ለእስራኤላውያንና ለጊዜውም ሆነ ለዘለቄታው በእስራኤል ለሚኖሩ መጻተኞች የመማጠኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ ባለማወቅ ተሳስቶ ሰው የሚገድል ማንኛውም ግለሰብ ከእነርሱ ወደ አንዱ አምልጦ መጠጋት ይችላል።


እርሱም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ፈጥኖ በመሄድ በከተማይቱ መግቢያ በር ወደሚገኘው ፍርድ ሸንጎ ቀርቦ የሆነውን ነገር ሁሉ ለመሪዎቹ ይገልጣል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ከተማይቱ እንዲገባ ይፈቅዱለታል፤ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡትና በዚያ ይቈያል፤


በሸንጎ ቀርቦ ፍርድ እስከሚቀበልና በዘመኑ ያለው ሊቀ ካህናት እስከሚሞትበት ጊዜ ድረስ በዚያች ከተማ ሊቈይ ይችላል፤ ከዚያም በኋላ ሸሽቶ ወደወጣበት ከተማ በመመለስ ወደ ቤቱ ይገባል።”


በምሥራቅ ዮርዳኖስ፥ ከኢያሪኮም በስተ ምሥራቅ ከፍ ብሎ በሚገኘው በረሓማ አገር፥ በሮቤል ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ቤጼርን፥ በጋድ ግዛት ውስጥ በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ግዛት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን መርጠው ለዩ፤


跟着我们:

广告


广告