Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 15:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚያም ድንበሩ ከተራራው ጫፍ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ምንጮች ይደርሳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ይወጣል፤ ወደ ባዓላ ወይም ቂርያት ይዓሪም ይታጠፋል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም በመቀጠል ከተራራው ዐናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች ዐልፎ ይወጣና ቂርያትይዓይሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቍልቍል ይወርዳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ድን​በ​ሩም ከተ​ራ​ራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄ​ዳል፤ ወደ ዔፍ​ሮ​ንም ተራራ ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኢያ​ሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደ​ር​ሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ፥ ቂርያትይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ደረሰ።

参见章节 复制




ኢያሱ 15:9
8 交叉引用  

ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ ዙፋኑን የዘረጋውን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ በዓለ ይሁዳ ሄዱ።


ዳዊትና ሕዝቡ ሁሉ በኪሩቤል ክንፎች ላይ የተቀመጠውን፥ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የአምላካቸውን የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ያመጡ ዘንድ በይሁዳ ግዛት ባዓላ ተብላ ወደምትጠራው ወደ ቂርያትይዓሪም ከተማ ሄዱ፤


በዓላ፥ ዒዩም፥ ዔጼም፥


ደግሞም ቂርያትባዓል ወይም ቂርያትይዓሪምና ራባ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው ያሉትን ትናንሽ ከተሞችን ይጨምራሉ።


የደቡቡም ድንበር በምዕራብ በኩል ከቂርያትይዓሪም መጨረሻ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ውሃ ምንጮች ያልፋል።


ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጒዞ ጀምረው ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሕዝብ ወደሚኖሩባቸው ከተሞች ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ በኤሮትና ቂርያትይዓሪም ተብለው ይጠሩ ነበር፤


እነርሱም ወጥተው በይሁዳ በምትገኘው ከቂርያትይዓሪም በስተ ምዕራብ ሰፈሩ፤ ያ ስፍራ እስከ አሁን የዳን ሰፈር ተብሎ የሚጠራውም ስለዚህ ነው።


በቂርያትይዓሪም ወደሚኖሩትም ሕዝብ መልእክተኞችን ልከው “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኛ አምጥተዋታልና መጥታችሁ ውሰዱት” አሉ።


跟着我们:

广告


广告