ኢያሱ 15:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም47 እንዲሁም በግብጽ ወሰን እስከሚገኘው ወንዝና እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ ድረስ የሚደርሱ ታናናሽ ከተሞችና መንደሮች ያሉአቸው አሽዶድና ጋዛ ተብለው የሚጠሩ ከተሞች ነበሩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም47 አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋራ፣ ጋዛ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋራ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)47 አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብጽ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)47 አሴያዶት መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም፥ ጋዛም መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕርም ወሰኑ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)47 አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ። 参见章节 |