Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 13:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በደጋማው አገር የሚገኙትን ከተሞችና መኖሪያውን በሐሴቦን አድርጎ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖንን ግዛት ሁሉ ይጨምራል። ሙሴም ንጉሥ ሲሖንንና የምድያም መሪዎች የነበሩትን፥ ኤዊን፥ ሬቄምን፥ ጹርን፥ ሑርንና ሬባዕን ድል ነሣ፤ እነዚህ ሁሉ ምድሪቱን የሚያስተዳድሩት የንጉሥ ሲሖን ገባሮች በመሆን ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ማለት በደጋው አገር የሚገኙት ከተሞች ሁሉና መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛውን የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት በሙሉ ያካትታል። ሙሴ ሴዎንንና በዚያው ምድር ተቀማጭ የነበሩትን መሳፍንት፤ ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር፣ ሑርና ሪባ የተባሉትን የምድያም አለቆች ድል አደረጋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንም የነገሠው የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም ሴዎንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የሴዎንን መሳፍንት፥ የምድያምን አለቆች ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርን፥ ሪባን ድል ነሣቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የሚ​ሶር ከተ​ሞች ሁሉ፥ በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገ​ሠው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም እር​ሱ​ንና በም​ድ​ሪቱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን የሴ​ዎ​ንን መሳ​ፍ​ንት፥ የም​ድ​ያ​ምን አለ​ቆች ኤዊን፥ ሮቦ​ቅን፥ ሱርን፥ ኡርን፥ ሮቤን በሲ​ዮን የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ገደ​ላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንም የነገሠው የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ሁሉ ነበረ፥ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የሴዎንን መሳፍንት፥ የምድያምን አለቆች ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርን፥ ሪባን መታቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 13:21
6 交叉引用  

የሴቲቱም ስም ኮዝቢ ይባል ነበር፤ “ጹር” ተብሎ የሚጠራው አባትዋም በአንድነት የሚኖሩ የጥቂት ምድያማውያን ጐሣዎች አለቃ ነበር።


አምስቱንም የምድያም ነገሥታት ኤዊን፥ ሬቄምን፥ ጹርን፥ ሑርንና ሬባዕን ገደሉ፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም ገደሉት።


በዚህም ዐይነት የባሳን ንጉሥ የዖግ ግዛቶች የሆኑትን በደጋ የሚገኙትን ሳለካና ኤድረዒ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና እንዲሁም የገለዓድንና የባሳንን አውራጃዎች ሁሉ ያዝን።


ቤትፐዖር፥ ከፒስጋ ተራራ በታች ያለው ረባዳ ምድርና ቤትየሺሞት ተብለው የሚጠሩትን ሁሉ ይጨምራል።


跟着我们:

广告


广告