ዮናስ 4:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ጥላ በማግኘት ከፀሐይ ግለት እንዲድን እግዚአብሔር አምላክ አንድ የቅል ተክል አብቅሎ ቅጠሎችዋ ከዮናስ ራስ በላይ እንዲሆኑ አደረገ፤ ዮናስም ከቅሉ ሐረግ ጥላ በማግኘቱ እጅግ ተደሰተ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እግዚአብሔር አምላክም የቅል ተክል አብቅሎ፣ የዮናስ ራስ ጥላ እንዲያገኝና ሙቀትም እንዳያስጨንቀው ከበላዩ እንዲያድግ አደረገ፣ ዮናስም ስለ ቅሉ እጅግ ደስ አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ጌታ እግዚአብሔርም የጉሎ ተክል አበቀለ፥ ከጭንቀቱም እንድታድነው፥ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ እንድትል አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ጉሎ ተክሉ እጅግ ተደሰተ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እግዚአብሔር አምላክም ቅልን አዘዘ፤ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው። 参见章节 |