Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 6:68 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

68 በዚህ ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃል አለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

68 ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ጌታ ሆይ፤ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

68 ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ! ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃል አለህ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

68 ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም የሕ​ይ​ወት ቃል እያ​ለህ ወደ ማን እን​ሄ​ዳ​ለን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

68 ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤

参见章节 复制




ዮሐንስ 6:68
17 交叉引用  

በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ? በምድርስ አንተን ካገኘሁ ሌላ ምን እሻለሁ?


በዚያን ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ፦ “አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ መሲሕ ነህ፤” ሲል መለሰለት።


“እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፦ “አንተ መሲሕ ነህ፤” ሲል መለሰለት።


እናንተስ፥ “እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፤ ጴጥሮስም፥ “አንተ የእግዚአብሔር መሲሕ ነህ፤” ሲል መለሰለት።


እኔ በራሴ ሥልጣን አልተናገርኩም፤ እኔ የምለውንና የምናገረውን ትእዛዝ የሰጠኝ የላከኝ አብ ነው።


የእርሱም ትእዛዝ የዘለዓለም ሕይወት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረው አብ የነገረኝን ነው።”


የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁ፤ እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ ዘንድ መጥቼ መምጣቴንም በእውነት ዐውቀዋል፤ አንተ እንደ ላክኸኝም አምነዋል።


“እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማና በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እርሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ስለ ሆነ አይፈረድበትም።


አዎ! የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያይና በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።”


ሕይወትን የሚሰጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሰው ኀይል ግን ለምንም አይጠቅምም፤ እኔ ለእናንተ የተናገርኩት ቃል መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው፤


“እናንተ ከአብርሃም ዘር የተወለዳችሁ ወንድሞችና እናንተም እግዚአብሔርን የምትፈሩ አሕዛብ! ይህ የመዳን ቃል የተላከው ለእኛ ነው።


ስለዚህ መዳን ከእርሱ በቀር በሌላ በማንም የለም፤ እኛ ልንድንበት የሚገባን እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ስም ከእርሱ በቀር በመላው ዓለም ማንም የለም።”


“ሂዱ! በቤተ መቅደስ ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝቡ ንገሩ!” አላቸው፤


በበረሓ ተሰብስቦ ከነበረው ሕዝብ ጋርና ከሲና ተራራ ላይ ከተናገረው መልአክ ጋር እንዲሁም ከአባቶቻችን ጋር የነበረው እርሱ ነው። የእግዚአብሔርን የሕይወት ቃል ለእኛ ያስተላለፈልንም ይኸው ሙሴ ነው።


ፊልጶስም “በሙሉ ልብህ ካመንክ መጠመቅ ትችላለህ” አለው። ጃንደረባውም “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምናለሁ” አለ።]


跟着我们:

广告


广告