Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 5:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማና በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እርሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ስለ ሆነ አይፈረድበትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃሌን የሚ​ሰማ በላ​ከ​ኝም የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ያገ​ኛል፤ ከሞ​ትም ወደ ሕይ​ወት ተሻ​ገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይ​ሄ​ድም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

参见章节 复制




ዮሐንስ 5:24
28 交叉引用  

ስለዚህ እነዚህ ወደ ዘለዓለም ቅጣት ሲሄዱ፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


ያመነና የተጠመቀ ይድናል፤ የማያምን ግን ይፈረድበታል።


በሕይወት የሚኖርና በእኔም የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽ?” አላት።


ኢየሱስም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “በእኔ የሚያምን በእኔ ብቻ ሳይሆን፥ በላከኝም ያምናል፤


ነገር ግን ኢየሱስ መሲሕ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንድታምኑና፥ አምናችሁም በእርሱ ስም የዘለዓለም ሕይወትን እንድታገኙ ይህ ተጽፎአል።


“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ዓለምን እጅግ ስለ ወደደው አንድያ ልጁን ሰጠ።


“በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ ቀድሞውኑ ተፈርዶበታል።


በወልድ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በእርሱ ላይ ይኖርበታል እንጂ ሕይወትን አያገኝም።


የሚያጭድ ደመወዙን ይቀበላል፤ ለዘለዓለም ሕይወት የሚሆን ፍሬም ይሰበስባል፤ ስለዚህ የሚዘራውም፥ የሚያጭደውም አብረው ይደሰታሉ።


አዎ! የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያይና በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።”


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ (በእኔ) የሚያምን ሰው የዘለዓለም ሕይወት አለው።


ከሰማይ የወረደው እንጀራ ይህ ነው፤ ይህን እንጀራ የሚበላ በፍጹም አይሞትም።


ከሰማይ የወረደው ሕይወትን የሚሰጥ እንጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ሁሉ ለዘለዓለም ይኖራል፤ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን እኔ የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።”


እንግዲህ ከሰማይ የወረደው እንጀራ ይህ ነው፤ እርሱም አባቶቻችሁ እንደ በሉት ዐይነት አይደለም፤ ያን እንጀራ የበሉ ሞተዋል፤ ይህን እንጀራ የሚበሉ ግን ዘለዓለም ይኖራሉ።”


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ፈጽሞ አይሞትም።”


ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖሩ አሁን ኲነኔ የለባቸውም።


እግዚአብሔር የጠራን ለቊጣ ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት መዳንን እንድናገኝ ነው።


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።


እናንተም በመጨረሻው ቀን ለሚገለጠው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።


እኛ ወንድሞቻችንን ስለምንወድ ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገራችንን እናውቃለን። ፍቅር የሌለው ሰው በሞት ጥላ ውስጥ ይኖራል።


ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን የሚያምን ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ አባቱን የሚወድ ሁሉ ልጁንም ይወዳል።


跟着我们:

广告


广告