Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 5:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይህን ነገር በሰንበት ስላደረገ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ኢየሱስን ያሳድዱት ጀመር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አይሁድም፣ በሰንበት ቀን እነዚህን ድርጊቶች በመፈጸሙ፣ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለዚህም አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር፤ በሰንበት ይህን አድርጎ ነበርና።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ያሳ​ድ​ዱ​ትና ሊገ​ድ​ሉ​ትም ይሹ ነበር፤ በሰ​ን​በት እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበ​ርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር።

参见章节 复制




ዮሐንስ 5:16
15 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እጀ ሽባውን “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋው ጊዜ እጁ ድኖ ልክ እንደ ደኅነኛው እጅ ሆነለት።


ወዲያውኑ ፈሪሳውያን ወጥተው እንዴት አድርገው ኢየሱስን እንደሚያጠፉት ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ተማከሩ።


የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ግን በጣም ተቈጥተው በኢየሱስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተመካከሩ።


የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ወደ ዮሐንስ ልከው፦ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ባስጠየቁት ጊዜ የሰጠው ምስክርነት የሚከተለው ነው፤


እነርሱም እንደገና ሊይዙት ፈለጉ፤ እርሱ ግን ከእጃቸው አምልጦ ሄደ።


አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን አስታውሱ፤ እኔን ካሳደዱኝ እናንተንም ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ከጠበቁ ቃላችሁንም ይጠብቃሉ።


ስለዚህ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ያንን የዳነውን ሰው “ዛሬ ሰንበት ስለ ሆነ አልጋህን እንድትሸከም ሕግ አይፈቅድልህም” አሉት።


ሰውየው ግን ሕዝብ ስለ በዛና ኢየሱስም ከዚያ ራቅ ብሎ ስለ ሄደ ያዳነው ማን እንደ ሆነ አያውቅም ነበር።


ሰውየውም ሄደና ያዳነው ኢየሱስ መሆኑን ለአይሁድ ባለሥልጣኖች ነገረ።


ኢየሱስ ግን “አባቴ ሁልጊዜ ይሠራል፤ እኔም እሠራለሁ” ሲል መለሰላቸው።


ይህም አባባል የአይሁድን ባለሥልጣኖች ኢየሱስን እንዲገድሉት በይበልጥ አነሣሣቸው፤ ይህም የሆነው እርሱ ሰንበትን በመሻሩ ብቻ ሳይሆን “እግዚአብሔር አባቴ ነው” በማለት ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ስለ አስተካከለ ነው።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ አንድ ሥራ ሠራሁ፤ እናንተም ሁላችሁ በዚህ ሥራ ትደነቃላችሁ።


ከኢየሩሳሌም ሰዎች አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፦ “ሊገድሉት የሚፈልጉት ሰው ይህ አይደለምን?


跟着我们:

广告


广告