Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 19:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች፥ የተሰቀሉትን ሰዎች ጭን ሰብረው፥ አስከሬናቸውን ከመስቀል እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት የሰንበት ዝግጅት ቀን ስለ ነበረና ያ ሰንበትም ትልቅ በዓል ስለ ሆነ፥ በሰንበት ቀን ሥጋቸው በመስቀል ላይ እንዳይሆን ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ዕለቱ ለሰንበት መዘጋጃ ቀን ነበር። አይሁድ፣ የተሰቀሉት ሰዎች ሬሳ በሰንበት ቀን በመስቀል ላይ እንዳይውል ስለ ፈለጉና ያም የተለየ ሰንበት ስለ ነበር፣ የተሰቀሉት ሰዎች ጭናቸው ተሰብሮ በድናቸው እንዲወርድ ጲላጦስን ለመኑት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ እንዲሁም ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና፥ ሥጋቸው በሰንበት ቀን በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 አይ​ሁድ ግን የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበ​ርና፥ የዚ​ያች ሰን​በ​ትም ቀን ታላቅ ናትና “ሥጋ​ቸው በሰ​ን​በት በመ​ስ​ቀል ላይ አይ​ደር” አሉ፤ ጭን ጭና​ቸ​ው​ንም ሰብ​ረው ያወ​ር​ዷ​ቸው ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።

参见章节 复制




ዮሐንስ 19:31
12 交叉引用  

ከዚያም ሰባት ቀኖች በመጀመሪያውና በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፤ በነዚያም ቀኖች ምግባችሁን ከማዘጋጀት በቀር ምንም ሥራ አትሠሩም።


ደግ ሰው ለቤቱ እንስሳት ይራራል፤ የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።


የሕዝቤን ቆዳ ገፋችሁ አጥንታቸውን ቈራርጣችሁ ለአፍላልና ለድስት እንደሚቈራረጥ ሥጋ አደረጋችኋቸው፤ ሥጋቸውንም በላችሁ።


በማግስቱ ቅዳሜ፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን በአንድነት ወደ ጲላጦስ ሄዱና እንዲህ አሉት፦


ቀኑ መሽቶ ስለ ነበር የሰንበት ዋዜማና የዝግጅትም ጊዜ ሆነ፤


ከዚህ በኋላ ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው።


የፋሲካ በዓል የዝግጅት ቀን ነበረ፤ ጊዜውም ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ፤ በዚያን ጊዜ ጲላጦስ አይሁድን “እነሆ ንጉሣችሁ!” አላቸው።


የሰንበት ዝግጅት ቀን ስለ ነበረና መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበረ የኢየሱስን አስከሬን እዚያ ቀበሩት።


የዐይንም ከተማ ንጉሥ በእንጨት ላይ ሰቅሎ ሬሳው እስከ ማታ ተንጠልጥሎ እንዲቈይ አደረገ። ፀሐይም በምትጠልቅበት ጊዜ ሬሳው ከተሰቀለበት እንጨት ላይ ወርዶ በከተማይቱ ቅጽር በር መግቢያ እንዲጣል አደረገ፤ በእርሱም ላይ ብዙ የድንጋይ ቊልል ከመሩበት፤ የድንጋዩም ቊልል እስከ አሁን በዚያው ይገኛል።


跟着我们:

广告


广告