Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 19:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉም ነገር እንደ ተፈጸመ ዐውቆ በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውም ቃል እንዲፈጸም “ተጠማሁ!” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ከዚያም ኢየሱስ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ ዐውቆ፣ የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም፣ “ተጠማሁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከወዲሁ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉም ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተጠማሁ” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሁሉ እንደ ተፈ​ጸመ ባየ ጊዜ የመ​ጽ​ሐፉ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ “ተጠ​ማሁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፦ “ተጠማሁ” አለ።

参见章节 复制




ዮሐንስ 19:28
14 交叉引用  

ጒሮሮዬ እንደ ሸክላ ደረቀ፤ ምላሴም ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤ እንደ ሞተ ሰው በትቢያ ላይ ተውከኝ።


በምግቤ ውስጥ ሐሞት ቀላቀሉ፤ በጠማኝም ጊዜ ሆምጣጤ ሰጡኝ።


ነገር ግን እኔ የምጠመቀው የመከራ ጥምቀት አለኝ፤ እርሱም እስኪፈጸም ድረስ ዕረፍት የለኝም።


ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ! ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ ስለ ሰው ልጅ በነቢያት የተጻፈው ሁሉ በዚያ ይፈጸማል።


ስለ እኔ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም ስለሚገባው ‘ከዐመፀኞች ጋር ተቈጠረ’ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል በእኔ ላይ መፈጸም አለበት እላችኋለሁ።”


በክብር ተገልጠው ይነጋገሩ የነበሩትም፥ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም መከራ እንደሚቀበልና እንደሚሞት ነበር።


እነሆ፥ ጊዜው ከአይሁድ ፋሲካ በዓል በፊት ነበር፤ ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት መድረሱን ዐወቀ። በዚህ በዓለም ያሉትን የራሱን ወገኖች ወዶአቸው ነበር፤ እስከ መጨረሻም ወደዳቸው።


እኔ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርኩህ።


ኢየሱስም የሚደርስበትን ሁሉ ዐውቆ ወደ እነርሱ ወጣ ብሎ “ማንን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው።


ስለዚህ ወታደሮቹ “ለማን እንደሚደርስ ለማወቅ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ፥ አንቅደደው” ተባባሉ። ይህም የሆነው፥ “ልብሴን ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉ” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ወታደሮቹም እንዲሁ አደረጉ።


ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከቀመሰ በኋላ “ተፈጸመ!” አለ። ራሱን ዘንበል አድርጎም ነፍሱን ሰጠ።


ይህም የሆነው፥ “ከእርሱ አንድ አጥንት እንኳ አይሰበርም” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው።


ስለ እርሱ የተጻፈውን ሁሉ ከፈጸሙበት በኋላ ከመስቀል አውርደው ቀበሩት፤


跟着我们:

广告


广告