Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 16:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “እስከ አሁን በምሳሌ ነገርኳችሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ በምሳሌ የማልናገርበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ስለ አብ ሁሉን ነገር ገልጬ እነግራችኋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “እስከ አሁን የነገርኋችሁ በምሳሌ ቢሆንም እንኳ፣ ከእንግዲህ ግን ስለ አብ በምሳሌ ሳይሆን በግልጽ የምናገርበት ጊዜ ይመጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ይህን በምሳሌ ነግሬአችኋለሁ፤ ነገር ግን ስለ አብ በምሳሌ ሳይሆን በግልጥ ለእናንተ የምናገርበት ሰዓት ይመጣል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “ዛሬስ በም​ሳሌ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን የአ​ብን ነገር ገልጬ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ለእ​ና​ንተ በም​ሳሌ የማ​ል​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ይመ​ጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ይህን በምሳሌ ነግሬአችኋለሁ፤ ነገር ግን ስለ አብ ለእናንተ በግልጥ የምናገርበት እንጂ ከዚያ ወዲያ በምሳሌ የማልናገርበት ሰዓት ይመጣል።

参见章节 复制




ዮሐንስ 16:25
19 交叉引用  

ሐሳቤን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፤ የምሳሌዎችንም ትርጒም በገና በመደርደር እገልጣለሁ።


ንግግሬን በምሳሌ እጀምራለሁ፤ ከጥንት ጀምሮ የተሰወረውን ምሥጢር እገልጣለሁ።


በዚህ ዐይነት ስውር የሆኑ የምሳሌዎችን ምሥጢር ጠቢባን የሚያቀርቡአቸውን እንቆቅልሾች መረዳት ያስችላሉ።


እኔ ግን “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ሁሉም ‘እርሱ ዘወትር የሚያስተምረው በምሳሌ ነው’ እያሉ ያጒረመርማሉ፤ ምን ይሻለኛል?” አልኩ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተም ይህ ምሳሌ አይገባችሁምን? ታዲያ፥ ሌሎችን ምሳሌዎች ሁሉ እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ?


ያለ ምሳሌም አያስተምራቸውም ነበር፤ ብቻቸውን ሲሆኑ ግን ሁሉን ነገር ለደቀ መዛሙርቱ ያስረዳቸው ነበር።


ይህን ነገር በግልጥ ነገራቸው፤ በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ለብቻው ገለል አድርጎት ይገሥጸው ጀመር። “እንዲህ አትበል” ሲል ተቈጣው።


በዚያን ጊዜ አይሁድ በዙሪያው ተሰብስበው፥ “እስከ መቼ በጥርጣሬ ታቈየናለህ? አንተ መሲሕ እንደ ሆንክ በግልጥ ንገረን” አሉት።


ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የተናገረውን አላስተዋሉም።


“ገና የምነግራችሁ ብዙ ነገር አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ይከብዳችኋል፤


ከምኲራቦች አስወጥተው ያባርሩአችኋል፤ እንዲያውም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።


ይሁን እንጂ እያንዳንዳችሁ በየበኩላችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ ሰዓቱም አሁን ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።


ስውርና አሳፋሪ የሆነውን ነገር አስወግደናል፤ በተንኰልም አንሠራም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አንለውጥም፤ ይልቅስ እውነትን በይፋ እናሳያለን፤ ራሳችንንም ለሰው ሁሉ ኅሊና በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ እናደርጋለን።


跟着我们:

广告


广告