ዮሐንስ 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በዚያን ጊዜ ከአይሁድ ብዙዎች ኢየሱስ በቢታንያ መሆኑን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ስለ ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 በዚህ ጊዜ ብዙ አይሁድ ኢየሱስ በዚያ መኖሩን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ኢየሱስን ብለው ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ከአይሁድም ብዙ ሰዎች በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፤ የመጡትም በኢየሱስ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ከአይሁድም ብዙ ሰዎች ጌታችን ኢየሱስ በዚያ እንዳለ በዐወቁ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፤ የመጡትም ጌታችን ኢየሱስን ለማየት ብቻ አልነበረም፤ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ለይቶ ያስነሣዉን አልዓዛርንም ያዩ ዘንድ ነበር እንጂ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ከአይሁድም ብዙ ሕዝብ በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፥ ከሙታንም ያስነሣውን አልዓዛርን ደግሞ እንዲያዩ ነበረ እንጂ ስለ ኢየሱስ ብቻ አይደለም። 参见章节 |