Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 12:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ኢየሱስም እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤ “ከእንግዲህ ለጥቂት ጊዜ ብርሃን አለላችሁ፤ ጨለማ ሳይመጣባችሁ፣ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ኢየሱስም “ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ ገና ለጥ​ቂት ጊዜ ብር​ሃን ከእ​ና​ንተ ጋር ነው፤ በጨ​ለማ የሚ​መ​ላ​ለስ የሚ​ሄ​ድ​በ​ትን አያ​ው​ቅ​ምና ጨለማ እን​ዳ​ያ​ገ​ኛ​ችሁ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ ተመ​ላ​ለሱ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ኢየሱስም፦ “ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።

参见章节 复制




ዮሐንስ 12:35
27 交叉引用  

የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ይወድቃሉ፤ የመውደቂያቸው ምክንያት ምን እንደ ሆነ አያውቁም።


እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! ኑ! በእግዚአብሔር ብርሃን እንመላለስ!


ስለዚህም መንገዳቸው የሚያዳልጥ መሬት ይሆናል፤ በጨለማም ሲራመዱ መንገዳቸውን ስተው ይወድቃሉ፤ በሚቀጡበትም ቀን ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ሰዎቹም “እነሆ! የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ በኩል እያለፈ ነው” ብለው ነገሩት።


ነገር ግን በሌሊት የሚመላለስ ብርሃን ስለሌለው ይሰናከላል።”


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ያለው ጊዜ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ አይሰናከልም።


የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃን እመኑ።” ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ሄደና ተሰወረባቸው።


በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።


“ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ እንደገናም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ።”


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ከእናንተ ጋር ጥቂት ጊዜ እቈያለሁ፤ ከዚያ በኋላ ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤


እንደገናም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ እኔን የሚከተል ሁሉ የሕይወት ብርሃን ያገኛል፤ በጨለማም አይመላለስም” ሲል ተናገራቸው።


የእነርሱ ልቡና በእርግጥ ደንዝዞአል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት ሲያነብቡ ልቡናቸው በዚያው መሸፈኛ እንደ ተሸፈነ ነው። ይህም የሚሆነው ያ መሸፈኛ የሚወገደው በክርስቶስ ብቻ ስለ ሆነ ነው።


ምቹ ጊዜ ካገኘን ለሰዎች ሁሉ ይልቁንም ለሚያምኑ ቤተ ሰዎች መልካም ነገርን እናድርግ።


ቀድሞ እናንተ በጨለማ ውስጥ ትኖሩ ነበር፤ አሁን ግን የጌታ ስለ ሆናችሁ ብርሃን ናችሁ ስለዚህ በብርሃን እንደሚኖሩ ሰዎች ተመላለሱ።


跟着我们:

广告


广告