Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 12:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 በዚያ የቆሙ ሰዎች ይህን በሰሙ ጊዜ፥ “ነጐድጓድ ነው!” አሉ። ሌሎች ደግሞ “መልአክ ነው የተናገረው!” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በዚያ የነበሩት፣ ድምፁን የሰሙት አያሌ ሰዎች፣ “ነጐድጓድ ነው” አሉ፤ ሌሎች ደግሞ፣ “መልአክ ተናገረው” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 በዚያ ቆመው የነበሩትም ሕዝብ በሰሙ ጊዜ “ነጐድጓድ ነው፤” አሉ፤ ሌሎች “መልአክ ተናገረው፤” አሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 በዚያ ቆመው ይሰሙ የነ​በሩ ሕዝብ ግን “ነጐ​ድ​ጓድ ነው” አሉ፤ “መል​አክ ተና​ገ​ረው” ያሉም አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 በዚያ ቆመው የነበሩትም ሕዝብ በሰሙ ጊዜ፦ “ነጐድጓድ ነው” አሉ፤ ሌሎች፦ “መልአክ ተናገረው” አሉ።

参见章节 复制




ዮሐንስ 12:29
12 交叉引用  

ለመሆኑ ኀይልህ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ኀይል የበረታ ነውን? ድምፅህስ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነውን?


በሦስተኛው ቀን ማለዳ የነጐድጓድ ድምፅ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭልጭታና ጥቅጥቅ ያለ ደመና በተራራው ላይ ታየ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የእምቢልታ ድምፅ ተሰማ። ሰዎቹም በሰፈሩበት ቦታ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።


ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤


ኪሩቤል በክንፎቻቸው የሚያሰሙት ድምፅ በውጪ በኩል ባለው አደባባይ እንኳ ይሰማ ነበር፤ ድምፁም ሁሉን የሚችል አምላክ ድምፅ ይመስል ነበር።


ከሳውል ጋር ይሄዱ የነበሩ ሰዎች ድምፅ እየሰሙ ማንንም ባለማየታቸው የሚናገሩትን አጥተው፥ ዝም ብለው ቆሙ።


በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።


ከሰማይም የታላቅ ፏፏቴ ውሃ ድምፅና ታላቅ ነጐድጓድ የመሰለ ከፍተኛ ድምፅ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ በገና ደርዳሪዎች በገና እየደረደሩ የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር።


ከዚህም በኋላ በጉ ከሰባቱ ማኅተሞች የመጀመሪያውን ሲከፍት አየሁ። ከአራቱ እንስሶች አንዱ እንደ ነጐድጓድ በሚያስገመግም ድምፅ “ና!” ሲል ሰማሁ።


ከዚህ በኋላ መልአኩ ጥናውን ይዞ ከመሠዊያው እሳት ሞላበትና ወደ ምድር ወረወረው፤ ነጐድጓድ፥ ድምፅ፥ መብረቅ፥ የምድር መናወጥም ሆነ።


跟着我们:

广告


广告