Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 9:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኔ ንጹሕና እውነተኛ ነኝ፤ ነገር ግን አነጋገሬ በደለኛ ያደርገኛል፤ የምናገራቸው ንግግሮች ሁሉ ይፈርዱብኛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ንጹሕ ብሆን እንኳ፣ አንደበቴ ይፈርድብኛል፤ እንከን የለሽ እንኳ ብሆን፣ በደለኛ ያደርገኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጻድቅ ብሆን እንኳን አፌ ይወቅሰኛል፥ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጻድቅ ብሆን አፌ ይወ​ቅ​ሰ​ኛል፤ ፍጹ​ምም ብሆን ጠማማ ያደ​ር​ገ​ኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጻድቅ ብሆን አፌ ይወቅሰኛል፥ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።

参见章节 复制




ኢዮብ 9:20
24 交叉引用  

ዑፅ ተብላ በምትጠራ አገር ኢዮብ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ከክፉ ነገር ሁሉ ርቆ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ምንም ነውር የሌለበት፥ ቅን ሰው ነበር።


ኃጢአት ብሠራ ወዲያው ችግር ውስጥ እወድቃለሁ ደግ ነገር ብሠራም አልመሰገንም ተጐሣቊዬ ኀፍረት ደርሶብኛል።


በከረጢት ታሽጎ እንደሚወረወር ጒድፍ በደሌን ሁሉ ታስወግድልኛለህ ኃጢአቴንም ትደመስስልኛለህ።


‘ኢዮብ የሚናገረው ያለ ዕውቀት ነው፤ ንግግሩም ፍሬ ቢስ ነው’


ኢዮብ ሆይ! በከንቱ ንግግር ታበዛለህ፤ ያለ ዕውቀትም ባዶ ቃላትን ትለፈልፋለህ።”


‘በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ሊገኝ የሚችል ሰው አለን? ወይስ በፈጣሪው ፊት ንጹሕ የሚሆን ሰው ይገኛልን?


ንጹሕ ሆኜ ብገኝ እንኳ፥ ፈራጁ አምላክ እንዲምረኝ እለምነዋለሁ እንጂ መልስ ልሰጠው አልደፍርም።


“አዎ! እኔ ይህ እውነት መሆኑን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ እንዴት ጻድቅ መሆን ይችላል?


እግዚአብሔር ንጹሕ አድርጎ እንደማይቈጥረኝ ስለማውቅ፥ መከራና ሥቃይ ይመጣብኛል ብዬ እፈራለሁ።


እንግዲህ በደለኛ ሆኜ ከተቈጠርኩ፥ በከንቱ መድከሜ ለምንድን ነው?


ኃጢአታችንን ብትከታተል ማን ከፍርድ ሊያመልጥ ይችላል?


በአንተ ፊት ማንም ጻድቅ ሰው ስለሌለ እኔን አገልጋይህን ለፍርድ አታቅርበኝ።


ከብዙ ንግግር ውስጥ ስሕተት አይጠፋም፤ ስለዚህ አስተዋይ ሰው ብዙ ከመናገር ይቈጠባል።


ጠማማ ልብ ያለው አይበለጽግም፤ አንደበቱ አታላይ የሆነ ሰው ችግር ላይ ይወድቃል።


እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።


የሕግ መምህሩ ግን ራሱን ጻድቅ ለማድረግ ፈልጎ፥ “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው።


እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ራሳችሁን በሰው ፊት ጻድቅ ታስመስላላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ፊት ክብር ያለው መስሎ የሚታይ፥ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።”


አእምሮአቸው በረከሰና እውነት በጠፋባቸው ሰዎች የሚደረግ የማያቋርጥ ክርክርን ነው፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እግዚአብሔርን ማምለክ የሀብት ማግኛ ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል።


እኛ ሁላችን ብዙ ጊዜ እንሳሳታለን፤ በንግግሩ የማይሳሳት እርሱ ሰውነቱን መቈጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


跟着我们:

广告


广告