Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 9:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ንጹሕ ሆኜ ብገኝ እንኳ፥ ፈራጁ አምላክ እንዲምረኝ እለምነዋለሁ እንጂ መልስ ልሰጠው አልደፍርም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ጻድቅ ብሆንም እንኳ፣ ልመልስለት አልችልም፤ ዳኛዬን ምሕረት ከመለመን ሌላ ላደርግ የምችለው የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጻድቅ ብሆንም እንኳን ልመልስለት አልችልም፥ ፈራጄን እማጸናለሁ እንጂ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በጽ​ድቅ ብጠ​ራው፥ ባይ​ሰ​ማ​ኝም፥ የእ​ር​ሱን ፍርድ እለ​ም​ና​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ጻድቅ ብሆን ኖሮ አልመልስለትም ነበር፥ ወደ ፈራጄም እለምን ነበር።

参见章节 复制




ኢዮብ 9:15
18 交叉引用  

እግዚአብሔርም የምናሴን ጸሎት ሰማ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመልሶ እንደገና እንዲገዛ ፈቀደለት፤ በዚህም ምናሴ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ መሆኑን ተገነዘበ።


ኃጢአት ብሠራ ወዲያው ችግር ውስጥ እወድቃለሁ ደግ ነገር ብሠራም አልመሰገንም ተጐሣቊዬ ኀፍረት ደርሶብኛል።


እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ በእኔ ላይ ያለህን ቅርታ ግለጥልኝ እንጂ አትፍረድብኝ!


ወደ እርሱም በምትጸልይበት ጊዜ የለመንከውን ሁሉ ስለሚፈጽምልህ፥ ስለትህን ትከፍላለህ።


በዚያ ቅን ሰው ከእርሱ ጋር ይከራከራል፤ ዳኛዬ እግዚአብሔርም ለዘለዓለም ነጻ ያወጣኛል።


አንድ ጊዜ፥ ወይም ሁለት ጊዜ ተናገርኩ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከቶ አልናገርም። እግዚአብሔር


“እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ወደ እግዚአብሔር እማጠን ነበር፤ ችግሬን ሁሉ እገልጥለት ነበር።


ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ብትመለስ፥ ሁሉን ቻዩን አምላክ ብትለምነው፥


የእርሱን ስም ብጠራና መልስ ቢሰጠኝም እንኳ አቤቱታዬን ያዳምጣል ብዬ አላምንም።


እኔ ንጹሕና እውነተኛ ነኝ፤ ነገር ግን አነጋገሬ በደለኛ ያደርገኛል፤ የምናገራቸው ንግግሮች ሁሉ ይፈርዱብኛል።


ምንም እንኳ ፍጹም ብሆን ስለ ራሴ አላስብም ሕይወቴንም እጸየፈዋልሁ።


እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”


አምላክ ሆይ! እባክህ አድምጠኝ፤ የእኛን ችግርና በስምህ የምትጠራውን ከተማ ጥፋት ተመልከት፤ ወደ አንተ የምንጸልየው የአንተን ምሕረት በመተማመን እንጂ በእኛ መልካም ሥራ በመመካት አይደለም።


ማቅ ለብሼና ዐመድ ላይ ተቀምጬ በመጾም ጸሎቴንና ልመናዬን ለማቅረብ ፊቴን ወደ ጌታ እግዚአብሔር መለስኩ።


እኔ እንደማውቀው ከሆነ ኅሊናዬ አይወቅሰኝም፤ ይህም እኔ ንጹሕ መሆኔን አያስረዳም፤ ነገር ግን በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ብቻ ነው።


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራን ሲቀበል በጽድቅ ለሚፈርደው አምላክ ራሱን ዐደራ ሰጠ እንጂ አልዛተም።


跟着我们:

广告


广告