Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 5:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ድኾችን ከጠላቶቻቸው ሰይፍ ያድናቸዋል፤ ችግረኞችንም ከጨቋኞች እጅ ነጻ ያወጣቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ድኻውን ከአፋቸው ሰይፍ፣ ከኀይለኛውም እጅ ያድነዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ድሀውን ከአፋቸው ሰይፍ አንዲሁም ከኃያላን እጅ ያድነዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በጦ​ር​ነት ይጠ​ፋሉ፤ ደካ​ማ​ውም ከኀ​ያሉ እጅ ያመ​ል​ጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ድሀውንም ከአፋቸው ሰይፍ ከኃያሉም እጅ ያድነዋል።

参见章节 复制




ኢዮብ 5:15
19 交叉引用  

የግፈኛውን መንጋጋ ሰበርኩ፤ ነጥቆ የወሰደውንም ከአፉ አስጣልኩ።


ድኾችን በመጨቈን ወደ እግዚአብሔር እንዲጮኹ አድርገዋቸዋል፤ እግዚአብሔርም የድኾችን ጩኸት ሰምቶአል።


እግዚአብሔር በሥቃይ ላይ ያሉትን፥ ከሥቃይ ያድናቸዋል። በደረሰባቸውም መከራ ትምህርት ይሰጣቸዋል።


እርሱ ክፉ ሰዎች በሕይወት እንዲኖሩ አያደርግም፤ ለተጨቈኑ ሰዎች ግን በቅንነት ይፈርድላቸዋል።


ክፉዎች ብርሃን ተከልክለዋል፤ ለዐመፅ ያነሡአቸው ክንዶቻቸውም ተሰብረዋል።


ክፉዎች እንደ አንበሳ ያገሣሉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ እግዚአብሔር ግን ጥርሳቸውን ይሰባብራል።


አንበሳ አድኖ የሚበላውን ሲያጣ እንደሚሞት እነርሱም ይሞታሉ፤ የአንበሳይቱም ደቦሎች እንደሚበተኑ የእነርሱም ልጆች ይበተናሉ፤


እግዚአብሔር ከክፉ ምላስ ይጠብቅሃል፤ ጥፋት ቢመጣብህም አትፈራም።


አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የምስኪኖችን ጸሎት ትሰማለህ፤ ልመናቸውንም አድምጠህ ታበረታታቸዋለህ።


ችግረኞችንም ከሥቃያቸው አወጣቸው፤ እንደ በግ መንጋ የበዙ ልጆችንም ሰጣቸው።


ምክንያቱም እርሱ ሊገድሉት ከተዘጋጁ ሰዎች እጅ ሊያድነው ስለ ድኻ ሰው መብት ይከራከራል፤


እግዚአብሔር ሆይ! ለድኾች እንደምትፈርድ፥ ለተጨቈኑትም መብታቸውን እንደምታስከብር ዐውቃለሁ።


ጌታ ሆይ! ሁለመናዬ እንዲህ ብሎ ይናገራል፤ ተበዳዮችን ከበደለኛ የሚያድን፥ ድኾችንና ተጨቋኞችን ከነጣቂዎች የሚጠብቅ እንደ አንተ ያለ ማነው?


በሕዝቡ መካከል ለተጨቈኑት ፍርድን ይስጥ፤ ችግረኞችንም ይርዳ፤ ጨቋኝንም ይደምስስ


ናቡከደነፆር የክብር ዘብ አዛዡን ናቡዛርዳንን እንዲህ ሲል አዘዘው፤


እግዚአብሔርም ለዳንኤል በሹሙ ፊት ሞገስን ሰጥቶ ልቡን አራራለት።


跟着我们:

广告


广告