Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 42:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ከኢዮብ ጋር እነዚህን ነገሮች ከተነጋገረ በኋላ ቴማናዊውን ኤሊፋዝን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ስለ እኔ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ትክክለኛውን ነገር ስላልተናገራችሁ እኔ በአንተና በሁለቱ ጓደኞችህ ላይ ተቈጥቼአለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር ይህን ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ፣ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፤ “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር ስላልተናገራችሁ፣ ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታም ይህንን ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ፥ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፦ “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና ቁጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዶአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ቃል ለኢ​ዮብ ከተ​ና​ገረ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቴማ​ና​ዊ​ውን ኤል​ፋ​ዝን እን​ዲህ አለው፥ “እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ኢዮብ አን​ዲት ቅን ነገ​ርን በፊቴ አል​ተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ምና አን​ተና ሁለቱ ባል​ን​ጀ​ሮ​ችህ በድ​ላ​ች​ኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔርም ይህን ቃል ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ እግዚአብሔር ቴማናዊውን ኤልፋዝን፦ እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዶአል።

参见章节 复制




ኢዮብ 42:7
13 交叉引用  

እግዚአብሔር ሰይጣንን “አገልጋዬን ኢዮብን ልብ ብለህ አየኸውን? እርሱን የመሰለ ታማኝና ደግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም፤ እርሱ ከክፋት ሁሉ ርቆ እኔን የሚፈራ ቀጥተኛ ሰው ነው” አለ።


ናዕማታዊውም ጾፋር እንዲህ አለ፦


የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ፥ የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድና የናዕማ አገር ሰው የሆነው ጾፋር፥ እነዚህ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ነበሩ። እነርሱም በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሥቃይ በሰሙ ጊዜ ሐዘናቸውን ሊገልጹለትና ሊያጽናኑት ከየአገራቸው ተጠራርተው በአንድነት ወደ ኢዮብ መጡ።


አንተም ቅን ልብ ያለህ ብትሆን እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ እጆችህም ከበደል ሥራ የነጹ ቢሆኑ እግዚአብሔር ይታደግሃል።”


ሦስቱ ሰዎች ለኢዮብ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት አለመቻላቸውን በማየቱ እጅግ ተቈጣ።


የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ፦


ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፦


ከዚህ በኋላ ኢዮብ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፦


ከዚህም የተነሣ የተናገርኩት ነገር ስላሳፈረኝ በዐመድና በትቢያ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”


የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድ እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦


እኔ ያመፅኩት በአንተ ላይ ነው፤ የበደልኩትም አንተን ብቻ ነው፤ አንተ የምትጠላውን ነገር አደረግሁ፤ ስለዚህ በእኔ ላይ መፍረድህና እኔንም መቅጣትህ ትክክል ነው።


跟着我们:

广告


广告