Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 39:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ንስርን ወደ ላይ ወጥቶ በከፍተኛም ቦታ ላይ ጎጆውን የሚሠራው አንተ አዘኸው ነውን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ንስር ወደ ላይ የሚመጥቀው፣ ጐጆውንም በከፍታ ላይ የሚሠራው፣ በአንተ ትእዛዝ ነውን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ንስር ከፍ ከፍ የሚለው፥ ቤቱንም በከፍታ ላይ የሚያደርገው በአንተ ተእዛዝ ነውን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በአ​ፍህ ትእ​ዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላ​ልን? ጆፌ አሞ​ራስ ልጆ​ቹን አቅፎ ያድ​ራ​ልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን? ቤቱንስ በአርያም ላይ ያደርጋልን?

参见章节 复制




ኢዮብ 39:27
11 交叉引用  

በውኑ ጭልፊት የሚያንዣብበው፥ ክንፎቹንም ወደ ደቡብ የሚዘረጋው በአንተ ጥበብ ነውን?


ንስር በቋጥኞች መካከል ይኖራል፤ እዚያም ጎጆውን ይሠራል። ቋጥኞቹም መከላከያ ይሆኑለታል።


በጐልማሳነቴ ሕይወቴን በመልካም ነገር ሁሉ ይሞላታል፤ እንደ ንስርም ወጣትነቴን ያድሳል።


“ ‘እኔ እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ ያደረግኹትንና ንስር ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ እንደምትሸከም እኔም እናንተን እስከዚህ ስፍራ እንዴት ወደ እኔ እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል፤


እንዲህ ዐይነቱ ሀብት እያየኸው ወዲያው ይጠፋል፤ በሰማይ እንደ ሚበርር ንስር ክንፍ አውጥቶ ይበራል።


እነርሱም፦ “በሰማይ የሚበር ንስር፥ በአለት ላይ የሚጐተት እባብ፥ በባሕር ላይ የሚጓዝ መርከብና ከሴት ጋር ፍቅር የያዘው ወንድ” ናቸው።


በእግዚአብሔር ተማምነው የሚኖሩ ግን ኀይላቸው ይታደስላቸዋል። እንደ ንሥር በክንፍ ይበራሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ አይደክሙም።


አለታማው ገደል ላይ የምትኖሪ፥ እስከ ተራራማው ጫፍ ድረስ የምትደርሽ ሆይ! ተፈሪነትሽና የልብሽ ኲራት አታለውሻል፤ ምንም እንኳ መኖሪያሽን እንደ ንስር ጎጆ ብታደርጊ እኔ ከዚያ ላይ አወርድሻለሁ ይላል እግዚአብሔር።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና ሕጌን ስለ ተላለፉ በቤቴ ላይ ጠላት እንደ ጆፌ አሞራ ያንዣበበ ስለ ሆነ የማስጠንቀቂያ መለከት ንፉ!”


“ከወፎች ወገን ልትጸየፏቸው የሚገባና የማይበሉ እነዚህ ናቸው፤ ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጪ፥


ነገር ግን እንደ ንስር ወደ ላይ ብትበር፥ መኖሪያህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ። ይህን እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”


跟着我们:

广告


广告