Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 39:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለ ብርቱ ጥንካሬው በእርሱ ትተማመናለህን? ከባድ ሥራህንስ ለእሱ ትተውለታለህን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጕልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለርሱ ትተዋለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጉልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ በእርሱ ትታመናለህን? አድካሚ ሥራህን ለእርሱ ትተዋለህን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጕል​በ​ቱስ ብርቱ ስለ​ሆነ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን? ተግ​ባ​ር​ህ​ንስ ለእ​ርሱ ትተ​ዋ​ለ​ህን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ጕልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ ትታመነዋለህን? ተግባርህንስ ለእርሱ ትተዋለህን?

参见章节 复制




ኢዮብ 39:11
16 交叉引用  

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ሰውን በመልካችንና በአምሳያችን እንፍጠር፤ ሰዎችም በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎች፥ በእንስሶችና በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች፥ እንዲሁም በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ።


እግዚአብሔርም “ብዙ፤ ተባዙ፤ ዘራችሁ ምድርን ይሙላ፤ ምድርም በቊጥጥራችሁ ሥር ትሁን፤ በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ” ብሎ ባረካቸው።


የዮሴፍ ወንድሞች የገዙትን እህል በአህዮቻቸው ጭነው ጒዞ ጀመሩ።


እንስሶች፥ ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና ዓሣዎች ሁሉ እናንተን በመፍራትና በመደንገጥ ይኑሩ፤ ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ።


ጐሽን ጠምደህ ሞፈር እየጐተተ እንዲያርስ ልታደርገው ትችላለህን?


ወደ አንተ እንደሚመለስና ሰብልህን ወደ አውድማ እንደሚያመጣልህ ትተማመንበታለህን?


ከብቶቻችን የሰቡ ይሁኑ፤ ሳይጨነግፉም በመርባት ይብዙ፤ በመንገዶቻችን የሐዘን ጩኸት ከቶ አይሰማ።


የእርሱ ደስታ በብርቱ ፈረሶችና፤ በጦረኞች ኀይል አይደለም።


አንዳንዶች በጦር ሠረገሎቻቸው፥ ሌሎችም በፈረሶቻቸው ይመካሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ኀይል እንታመናለን።


የምታርስባቸው በሬዎች ከሌሉህ ጐተራህ ባዶ ይሆናል። በሬዎች ካሉህ ግን ጐተራህ በእህል የተሞላ ይሆናል።


በዚህ ፈንታ በፈጣን ፈረሶች ላይ ተቀምጣችሁ ከጠላቶቻችሁ እጅ ለማምለጥ ታቅዳላችሁ፤ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ‘ፈረሶቻችን እጅግ ፈጣኖች ናቸው’ ትሉ ይሆናል፤ ነገር ግን አሳዳጆቻችሁ ከእናንተ የፈጠኑ ይሆናሉ።


በደቡባዊ በረሓ ስለሚኖሩ እንስሶች የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ “መልእክተኞቹ የአንበሶች መኖሪያ፥ የመርዘኛ እባቦችና የበራሪ ዘንዶዎች መስለክለኪያ በሆነ አደገኛ አገር አቋርጠው ይሄዳሉ፤ በአህዮቻቸውና በግመሎቻቸው ውድ የሆኑ ስጦታዎችን ጭነው ምንም ርዳታ ልትሰጣቸው ወደማትችል አገር ይሄዳሉ።


“ቤልና ኔቦ የተባሉት የሐሰት አማልክት ያጐነብሳሉ፤ ጣዖቶቻቸው በጭነት እንስሶች ላይ ተጭነዋል፤ የተጫኑት ምስሎች ለደካማ እንስሳ ከባዶች ናቸው።


ከግብጽ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር እርሱ ለእነርሱ እንደ ጎሽ ቀንድ ይዋጋላቸዋል፤


跟着我们:

广告


广告