Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 38:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ዝናብንና ጤዛን የሚያስገኝ ማነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ዝናብ አባት አለውን? የጤዛን ጠብታ ማን ወለደው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይም የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የዝ​ናብ አባቱ ማን ነው? ወይስ የጠ​ልን ነጠ​ብ​ጣብ የወ​ለደ ማን ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው?

参见章节 复制




ኢዮብ 38:28
22 交叉引用  

እግዚአብሔር ከሰማይ የሚያረሰርስ ጠል ይስጥህ! ምድርህን ያለምልምልህ! እህልህንና ወይንህን ያብዛልህ!


ይስሐቅም እንዲህ አለው፤ “በረከት ከሞላበት ለምለም ምድር ርቀህ ትኖራለህ፤ የሰማይ ጠልም አታገኝም፤


“እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።


በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ” አለው።


ሥሮቹ ዘወትር ውሃ እንደሚያገኙና ቅርንጫፎቹም በጠል እንደሚርሱ ዛፍ ነበርኩ።


“እግዚአብሔር ውሃን ከባሕር ወደ ላይ ይስባል፤ ከሰማይም ያዘንበዋል።


ከደመናው ዝናብ እየጐረፈ ይወርዳል፤ በሰዎችም ላይ በብዛት ይዘንባል።


“ከምድር ውስጥ ፈንድቶ በወጣ ጊዜ የመፍለቂያ በሮቹን የዘጋ ማነው?


እርሱ ደመናን በሰማይ ላይ ይዘረጋል፤ ለምድር ዝናብን ይሰጣል፤ ተራራዎችንም በለምለም ሣር ይሸፍናል።


በእርሱ ጥበብ ወንዞች ይፈስሳሉ፤ ደመናዎችም ለምድር ዝናብን ይሰጣሉ።


በእርሱ ትእዛዝ ከሰማይ በላይ ያሉ ውሃዎች የመናወጥ ድምፅ ያሰማሉ፤ እርሱ ደመናዎችን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ በዝናብ ጊዜም መብረቅ እንዲበርቅ ያደርጋል፤ ነፋስንም ከማከማቻው ይልካል።


ከአሕዛብ አማልክት መካከል አንዱ እንኳ ዝናብ ማዝነብ አይችልም፤ ሰማይም በራሱ ፈቃድ ካፊያ አያወርድም፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ስለ ሆንክ እኛ ተስፋ የምናደርገው በአንተ ነው።


የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በወቅቱ የምሰጣችሁ፥ የመከርንም ወራት በየዓመቱ የማመላልስላችሁ እኔ ነኝ፤ እናንተ ግን እኔን ማክበርን ተዋችሁ።


ለእስራኤል ሕዝብ እንደሚወርድ ጠል እሆናለሁ። እነርሱ እንደ አበባ ይፈካሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥር ይሰዳሉ።


“እናንተ የጽዮን ሕዝብ ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ እርሱ በትክክል ፈርዶ እንደ ወትሮው በበጋና በክረምት ወራት በቂ ዝናብ ሰጥቶአችኋል።


አዝመራችሁ ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ እንዲቋረጥ አደረግሁ፤ በአንድ ከተማ ሲዘንብ በሌላው ከተማ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ ለአንዱ እርሻ ሲዘንብለት ሌላው እርሻ ዝናብ አጥቶ ደረቀ።


ይህን ብታደርጉ፥ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣል፤ እንዲሁም ለጻድቃንና ለግፈኞች ዝናቡን ያዘንባል።


ስለ ዮሴፍም ነገድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከላይ በሰማይ በሚዘንብ ዝናብ፥ ከታችም ከጥልቀት በሚገኘው ውሃ፥ ምድራቸውን ይባርክ።


ስለዚህ የያዕቆብ ዘሮች ከሰማይ ጠል በሚወርድባት፥ እህልና የወይን ጠጅ በሞላባት ምድር ዋስትና አግኝተው በሰላም ይኖራሉ።


跟着我们:

广告


广告