Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 38:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ክፉዎች ብርሃን ተከልክለዋል፤ ለዐመፅ ያነሡአቸው ክንዶቻቸውም ተሰብረዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ክፉዎች ብርሃናቸውን ተከልክለዋል፤ ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሯል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከበደለኞች ብርሃናቸው ተከልክሎአል፥ ከፍ ያለውም ክንድ ተሰብሮአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የኃ​ጥ​ኣ​ንን ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ከል​ክ​ለ​ሃ​ልን? የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንስ ክንድ ሰብ​ረ​ሃ​ልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከበደለኞች ብርሃናቸው ተከልክሎአል፥ ከፍ ያለውም ክንድ ተሰብሮአል።

参见章节 复制




ኢዮብ 38:15
17 交叉引用  

ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ!” ብሎ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን ጸሎት በመስማት፥ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ።


ከብርሃን ወደ ጨለማ ይባረራል፤ ከሕያዋን ምድርም ይወገዳል።


“የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፤ የእሳቱም ነበልባል ዳግመኛ አይታይም።


“ብርሃንን የሚጠሉ ሰዎች አሉ፤ ብርሃንም ምን እንደ ሆነ ስለማያውቁ የብርሃንን መንገድ አይከተሉም።


ይህን ሁሉ ሳላደርግ ቀርቼ ከሆነ ክንዴ ከትከሻዬ ይውለቅ፤ ከመገናኛውም ተሰብሮ ይለይ፥


የንጋት ብርሃን ኰረብቶችንና ሸለቆዎችን እንደ ተጣጠፈ ልብስ ቈመው እንዲታዩ ያደርጋቸዋል፤ በሸክላ ላይ እንዳለ መኅተምም አጒልቶ ያሳየዋል።


ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ ገና በእኩለ ቀን፥ በሌሊት ጨለማ ውስጥ እንዳሉ ሆነው ይደናበሩ።


ድኾችን ከጠላቶቻቸው ሰይፍ ያድናቸዋል፤ ችግረኞችንም ከጨቋኞች እጅ ነጻ ያወጣቸዋል።


የኃጢአተኞችንና የክፉ ሰዎችን ኀይል አድክም፤ ከእንግዲህ ወዲያ ክፋትን እንዳያደርጉ በክፉ ሥራቸው ሁሉ ቅጣቸው።


የክፉዎች ኀይል ይሰበራል ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ያበረታቸዋል።


የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ይወድቃሉ፤ የመውደቂያቸው ምክንያት ምን እንደ ሆነ አያውቁም።


ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።


ከዚህም የተነሣ እኔ ጌታ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ እነሆ፥ እኔ የግብጽን ንጉሥ በቊጣ ተነሥቼበታለሁ፤ ስለዚህም ሁለት እጆቹን፥ ማለትም ከዚህ በፊት የተሰበረውንና ደኅነኛውን ጭምር ልሰብር ተዘጋጅቻለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።


“ነገር ግን የአገሩ ተወላጅም ሆነ መጻተኛ፥ ሆን ብሎ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ የንቀት ዝንባሌ በማሳየቱ ከሕዝቡ ይለይ፤


跟着我们:

广告


广告