Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 37:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “በውሽንፍሩም ኀይል ልቤ ተንቀጠቀጠ፤ በፍርሃትም ተርበደበደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ልቤ በዚህ በኀይል ይመታል፤ ከስፍራውም ዘለል ዘለል ይላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥ ከስፍራውም ውጭ ዘለለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ስለ​ዚ​ህም ልቤ ደነ​ገ​ጠ​ች​ብኝ፥ ከስ​ፍ​ራ​ዋም ተን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥ ከስፍራውም ተንቀሳቀሰ።

参见章节 复制




ኢዮብ 37:1
15 交叉引用  

እኔ እንኳ ሳስበው ያስደነግጠኛል፤ ሰውነቴንም በፍርሃት ያንቀጠቅጠዋል።


ነጐድጓድ፥ ኀይለኛ ዝናብ መምጣቱን ያመለክታል፤ እንስሶችም ውሽንፍር መምጣቱን ያውቃሉ።


ከአፉ የሚወጣውን ድምፅ ስሙ እንደ ነጐድጓድ የሚያጒረመርመውን ቃሉን አድምጡ።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር


ፍርሀትና መርበድበድ ይዞኝ፥ አጥንቶቼ ሁሉ እንዲንቀጠቀጡ አደረገ።


አንተን ከመፍራቴ የተነሣ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርድህንም እጅግ ፈራሁት።


በሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤ መካከል እግዚአብሔር የተፈራ ነው፤ በዙሪያውም ካሉት ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው።


በሦስተኛው ቀን ማለዳ የነጐድጓድ ድምፅ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭልጭታና ጥቅጥቅ ያለ ደመና በተራራው ላይ ታየ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የእምቢልታ ድምፅ ተሰማ። ሰዎቹም በሰፈሩበት ቦታ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።


እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ታዲያ ስለምን አታከብሩኝም? በፊቴስ ለምን አትንቀጠቀጡም፤ አሸዋን ውሃ አልፎት እንዳይሄድ ለዘለዓለሙ የባሕር ወሰን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ ባሕር የቱንም ያኽል ቢናወጥ፥ ማዕበል፥ ሞገዱም ቢያስገመግም፥ ወሰን የሆነውን የአሸዋ ግድብ አልፎ መሄድ አይችልም።


ይህን ሁሉ ስሰማ ሰውነቴ ይርበደበዳል፤ ድምፁም ከንፈሮቼን ያንቀጠቅጣል፤ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼ ከታች ይብረከረካሉ፤ በጠላቶቻችን ላይ መከራ የሚደርስበትን ጊዜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።


በድንገት የወህኒ ቤቱ መሠረት እስኪናጋ ድረስ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ በሮቹም ሁሉ በአንድ ጊዜ ተከፈቱ፤ የእያንዳንዱም እስረኛ ሰንሰለት ተፈታ።


በዚህ ጊዜ ጠባቂው መብራት አስመጥቶ እየሮጠ ወደ ውስጥ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ እግር ሥር በግንባሩ ተደፋ።


ስለ ዳንም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ዳን እንደ አንበሳ ደቦል ነው፤ እርሱ ከባሳን ይዘላል።”


跟着我们:

广告


广告